በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 የሚገኘው የቁስቋም ጣይቱ ብጡል የመጀመሪይና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ2018 ዓ.ም ልዩ ልዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 22, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

አንደኛ ዙር ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር ቁ/ጣ/ብ/የመጀመሪያና መካከለኛ ደ/ት/ቤት 001/2018

በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 የሚገኘው የቁስቋም ጣይቱ ብጡል የመጀመሪይና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት እና በወተመህ በጀት ግዥ ለመፈፀም የወጣ ጨረታ

  1. ለደንብ ልብስ ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ 28,793.00 ብር
  2. ለደንብ ልብስ ስፌት ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒአ 1,500.00 ብር
  3. አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎችና የቢሮ እቃዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ 18,200.00 ብር
  4. ለህትመት ጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ 700.00 ብር
  5. ለቀይ መስቀል ለመጀመሪያ ርዳታ እቃዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ 700.00 ብር
  6. አላቂ የትምህርት እቃዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒኦ 8,800.00 ብር
  7. አላቂ የፅዳት እቃዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ 24,700.00 ብር
  8. ለልዩ ልዩ መሳሪያዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ 1000.00 ብር
  9. ከሆቴል ውጪ መስተንግዶ ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ 30,000.00 ብር
  10. ለፕላንት ለማሽነሪ እና ለመሳሪያ እድሳትና ጥገና ሲፒኦ ብር 3,680.00
  11.  ለህንጻ ለቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች እድሳትና ጥገና ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ 3000.00 ብር
  12. ለህንጻ ለቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች እድሳትና ጥገና(በወተመህ) በጀት ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 5000.00
  13. ለፕላንት፤ ለማሽነሪ እና ለመሳሪያዎች መግዣ እቃዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒአ 3680.00 
  14. ለእቃ ጭነት አገልግሎት የሚውል ትራንስፖርት ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ 5000.00 ብር 

በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይፈልጋል።

  1. አግባብነት ያለው ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ።
  2. የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ።
  3. ከፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት ሊስት የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ በቁስቋም ጣይቱ ብጡል የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሚል ተሞልቶ ማቅረብ ይኖርበታል።
  5. ስለ ጨረታው የሚገልፀው የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በሎት በመከፈል ሰነዱን ከፋይናንስ ቢሮ መግዛት ይችላሉ። ጨረታው በ10ኛው ቀን 11፡30 ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም ባይገኙም በጨረታ ኮሚቴው አማካኝነት ይከፈታል።
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ መግለጫ በታሸገ ኤንቬሎፕ ኦርጅናል እና ኮፒ በማድረግ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  7. ተጫራቾች መጫረት የሚችሉት በንግድ ፍቃድ ዘርፍ ብቻ መሆን አሰበት
  8. ተጫራቾች በእያንዳንዱ ሳምፕል ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና(ሳምፕል)ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ቅድሚያ ናሙና ያላቀረቡ ተጫራቾች ከውድድሩ ውጪ ይሆናሉ።
  9.  አሸናፊው በሚያቀርባቸው እቃዎች ላይ 10% የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል።
  10. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸው እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት መስሪያ ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማድረስ ግዴታ አለበት።
  11. በማስታወቂያው ያልተገለጹ ነገሮች ቢኖሩም በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል።
  12. ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. ማንኛውም ተጫራቾች በሚያቀርቡበት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ቫትን አካቶ መቅረብ ይኖርባቸዋል።
  14. በዚህ ጨረታ ላይ ከተጠቀሰው ስራ (አቃ) ከውል በፊት እንዳአስፈላጊነቱ 20% መጨመር ወይም የመቀነስ ት/ቤቱ መብት ይኖረዋል።
  15. የጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራች በሚወዳደርበት እቃ ካደራጃቸው የመንግስት ተቋም ለግዥ ፈፃሚ መ/ቤት የተፃፈ ደብደቤ መያዝና ማወዳደር የሚችሉት በሚያመርቱት ምርት ላይ ብቻ ልዩ አስተያየት ይደረጋል ይህ ካልሆነ እንደማንኛውም ተወዳዳሪ እኩል ይወዳደራል።

አድራሻ፡- ሽሮሜዳ ከፍብሎ እንጦጦ ፓርክ መውጫ

ስልክ፡- 0111236202

የቁስቋም ጣይቱ ብጡል የመጀመሪያና መካከለኛ/ደ/ት/ቤት