በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን በእዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 22, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር፡- 002/2018 ዓ.ም

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን በእዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተለያዩ እስቴሽነሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች ማለትም፡-

1. ሎት 1 – የተለያዩ የፅሕፈት መሳሪያዎች፣

2. ሎት 2 – የተለያዩ ኤሌክትሮኒክሶች፣

3. ሎት 3 – የተለያዩ ፈርኒቸሮች፣

4. ሎት 4 – የተለያዩ ሞተሮች፣

5. ሎት 5 – የተለያዩ ጎማዎች፣

  1. በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላችሁና የዘመኑን ግብር በመክፈል ፈቃድ ያደሳችሁ እና ፈቃዳችሁን ኦላይን የተመዘገባእሁ።
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ።
  3. በዕቃ አቅራቢነት የተመዘገቡ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ተወዳዳሪዎች ለወረዳችን የቫት 7.50% የጀመርን እና ገቢ የምታደርድጉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ከጠቅላላ ገንዘብ ለሎት 1 – 20,000 (ሃያ ሺህ)፣ ለሎት 2 – 20,000 (ሀያ ሺህ)፣ ለሎት 3 – 15,000 (አስራ አምስት ሺህ)፣ ለሎት 4 – 20,000 (ሀያ ሺህ) እና ለሎት 5 -15,000 (አስራ አምስት ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (ጥሬ ገንዘብ) በእዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም ማቅረብ አለባችሁ፡፡
  6. ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸውን ዕቃዎች እዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት መጋዘን ድረስ አጠቃላይ በአንድ ጊዜ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  7. ተጫራቾች በእያንዳንዱን ሎት የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ዶክመንት ለመግዛት የሚያስችል የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ ሰነዳቸውን ፋይናንስ ጽ/ቤት ግ/ን/አስተዳደር ዋና የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 10 መውሰድ ትችላላችሁ፡፡
  8. ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀ ቀን ጀምሮ በ7 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ውል መፈፀም አለባቸው።
  9. ተጫራቾች በጨረታው ማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ7 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ውል ማስከበሪያ አሰርተው ውል ካልፈፀሙ መስሪያ ቤቱ የጨረታ ማስከበሪያውን የመውረስ መብት አለው፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማለትም ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀናት ጨምሮ አየር ላይ ይውላል። ጨረታው በዚህ እለት 8፡00 ሰዓት ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ። 
  11. ጨረታው በ15ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገርግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት ጨረታው ከመከፈት አያስተጓጉለውም።
  12. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። 
  13. ተጫራቾች የተጫረቱባቸውን እቃዎች ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው።
  14. ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት ፀንቶ ይቆያል።

ማሳሰቢያ፡ ወረዳው በጉራጌ ዞን ከወልቂጤ ከተማ 42 ኪ.ሜ ከአዲስ አበባ 197 ኪ.ሜ ላይ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09 13-37-12-45/ 09-23-13-37-39 እና 09-23-51-95 14

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት