በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 የሚገኘው የህብረት በልጅነት ቅድመ አንደኛ አና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2018 በጀት ዓመት ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 22, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 የሚገኘው የህብረት በልጅነት ቅድመ አንደኛ አና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  • ሎት-1 የደንብ ልብስ 4,500 ብር፣
  • ሎት-2 የፅህፈት መሳሪያ 3,500 ብር፣
  • ሎት-3 የፅዳት ዕቃዎች 5,500 ብር፣
  • ሎት-4 ቋሚ ዕቃዎች 5,000 ብር፣
  • ሎት-5 እድሳት 3,000 ብር፣
  • ሎት-6 ህትመት 1,100ብር፣
  • ሎት-7 የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች 1,200 ብር፣
  • ሎት-8 የማሽነሪ የጥገና 1,000 ብር፣
  • ሎት-9 ህከምና 120 ብር፣
  • ሎት-10 ልዩልዩ መሳሪያ 200 ብር፣
  • ሎት-11 የደንብ ልብስ ስፌት

በመሆኑም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን 16/12/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መግዛት ይቻላል።

  1. የአመቱ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፤
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎቶች ብር የተጠቀሰውን በባንክ በተመሰከረለት CPO ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዛችሁ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ሲወዳደሩ በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፤ ናሙና ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታ ውጪ ይሆናል፡፡
  6. ተጫራቾች በጨረታ ሲያሸንፉ ከጠቅላላ ዋጋ አስር ፐርሰንት (10%) የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች ጨረታ ሰነዱን ኮፒ በማድረግ ኦሪጅናሉን እና ኮፒውን በሁለት ፖስታ አሽገው ከጨረታ ሰነድ ጋር አብረው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች ሲጫረቱ እራሳቸው ባመረቱት ዕቃ ብቻ መሆን አለበት፡፡ ጨረታው ሲከፈት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል በተገኙበት ይሆናል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ29/12/2017 ዓ.ም በ4፡30 ሰዓት በት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ነው፡፡ ት/ቤቱ የተለየ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ የመሰረዘ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል፡፡

አድራሻ፡- አበበ ቢቂላ ስቴዲየም አጠገብ ወረዳ 05 ወጣት ማዕከል ገባ ብሎ

ስልክ ቁጥር፡- 011-213-8391/ 011-273-2447
የህብረት በልጅነት ቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት