Your cart is currently empty!
የበቾ ወረዳ ፍርድ ቤት ለመስሪያ ቤቱ የጽሕፈት መሳሪያዎችን፣ የጽዳት ዕቃዎችን፣ የደንብ ልብስ፣ የኤሌትሮኒክስ ዕቃዎችን ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 22, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግዥ ጨረታ ማስታወቅያ ቁጥር 01/2018
የበቾ ወረዳ ፍርድ ቤት ለመስሪያ ቤቱ የጽሕፈት መሳሪያዎችን፣ የጽዳት ዕቃዎችን፣ የደንብ ልብስ፣ የኤሌትሮኒክስ ዕቃዎችን ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ በጨረታው ላይ ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ሁሉ የዘመኑን የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች የዕቃዎችን ዝርዝር ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመከፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በደቡብ ምዕ/ሸዋ ዞን በበቾ ወረዳ ፍ/ቤት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 15 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ።
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ብር 3000 /ሦስት ሺህ/ በባንከ በተመሰከረለት ሲፕኦ ማስያዝ አለባቸው።
ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ከላይ በተራ ቁጥር 2 በተጠቀሰው አድራሻ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 5፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው በ16ኛ ቀን ከቀኑ በ 7፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተራ ቁጥር 2 በተገለጸው ቦታ ይከፈታል፡፡
በተራ ቁጥር 4 እና 5 ላይ የተገለፀው 16ኛው ቀን ዕለቱ የበዓል ቀን ላይ ከዋለ ወይም ዕለቱ ዝግ ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ላይ ይከፈታል።
አሸናፊው አሸናፊነቱ ከታወቀበት ቀን ጀምሮ እሰከ 10 ባሉ ቀናቶች በበቾ ወረዳ ፍርድ ቤት ቱሉ ቦሎ ከተማ ከ አ/አ 80 ኪ.ሜ ላይ በራሱ መጓጓዣ ዕቃዎችን አቅርቦ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
ተጫራቾች በጨረታው መሠረት እቃዎቹን ሙሉ ከአስረከቡ ክፍያው ወዲያውኑ ይፈፀማል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ ማብራርያ ከፈለጉ ስልክ ቁጥር 0113 421 269 / 0113 420 012 ደውለው ይጠይቁ ፡፡
የበቾ ወረዳ ፍርድ ቤት
ቱሉ ቦሎ