በአርሲ ዞን የጀጁ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ 2018 የበጀት ዓመት በወረዳ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 22, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

1ኛ የጨረታ ማስታወቂያ ቁ- C1-01/2018

በአርሲ ዞን የጀጁ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ 2018 የበጀት ዓመት በወረዳ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም፡-

  1. ለተጠየቁት የግዢ እቃዎች ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax Payer Registration No.) የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና በፌዴራል በክልል ወይም በዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ወይም በግዥዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው ዋናውናና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ ለጽሕፈት መሣሪያዎች እና ለመኪና ጎማዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 350.00 (ሶስት መቶ ሃምሳ) ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች እና ለደንብ ልብስ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) በጀጁ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000075254591 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጽ/ቤቱ የግዥ፤ ንብረት አስተዳደር፤ ማስወገድና ጠቅላላ አገ/ቢሮ ቁጥር 02 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡ 
  3. ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመክፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በማሟላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 16ኛ የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን፤ ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 5፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጽ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፤
  5. ማንኛውም ተጫራች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፤ ለፈርኒቸር እቃዎች እና ለጽሕፈት መሣሪያዎች ሰነድ ለእያንዳንዱ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ) ለደንብ ልብስ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 25.000.00 (ሃያ አምስት ሺህ) እንዲሁም ለመኪና ጎማዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30.000.00 (ሰላሳ ሺህ) በአቅራቢያቸው በሚገኝ በታወቀ ባንክ በክፍያ ማስያዥያ (CPO) ብቻ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. አሸናፊው ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የዕቃ ክምችት ያለውና እቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ አርቦ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል።
  7. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር፡- 09 16 52 27 62 ፣ 09 19 21 60 98፣ 09 20 07 69 02
09 20 40 24 52 ይጠይቁ።
የጀጁ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት