በማ/ኢ/ክ/መንግስት በስልጤ ዞን የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለአገልግሎት የሚያስፈልጉትን የተለያዩ ለቢሮ መገልገያ የሚሆኑ ዕቃዎችን ግዢ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 23, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

በማ/ኢ/ክ/መንግስት በስልጤ ዞን የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለአገልግሎት የሚያስፈልጉትን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ለቢሮ መገልገያ የሚሆኑ ዕቃዎችን ግዢ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የሚፈለጉ የዕቃ ዓይነቶች

  1. አላቂ የቢሮ ስቴሽነሪዎች
  2. የመኪና ጎማ
  3. የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
  4. ኢምፖርትድ ፈርኒቸር
  5. የውሃ ዕቃ
  6. የግንባታ ዕቃ
  7. የሞተር ሳይክል መለዋወጫ ዕቃ
  8. የደንብ ልብስ

በመሆኑም ተጫራች ድርጅቶች

  • በተሰማሩበት ዘርፍ ሕጋዊና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  •  የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢና ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ፣
  • የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
  • የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ማንኛውም ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ የማይመለስ 100 ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከአ/ው/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በመውሰድና በመሙላት መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ እንዲሁም ተጫራች ድርጅቶች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ሲፒኦ ለተራ ቁጥር 1፤2፤3፤4፤5፤6 እና 7 ለእያንዳንዳቸው 5,000 (አምስት ሺህ ብር)ለተራ ቁጥር 8 3,000 (ሦስት ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ በመሆኑም ጨረታው የሚከፈተው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከ15ኛው ቀን በኋላ ባለው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባልተገኙበት ከቀኑ በ6፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡
  • በተጨማሪም ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሰነድ ቴክኒክል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- 09 10 15 49 43 ወይም 09 17 01 03 09
የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት