Your cart is currently empty!
በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 09 አዲስ አምባ አፀደ ህፃናት የመ/ደ/ት/ቤት ለ2018 በጀት አመት ቋሚ ዕቃ፣ የደንብ ልብስ፣ አላቂ የጽዳት እቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች፣ ለተለያዩ መሳሪያዎች እና መፃህፍት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 23, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 09 አዲስ አምባ አፀደ ህፃናት የመ/ደ/ት/ቤት ለ2018 በጀት አመት የሚያስፈልጉ እቃዎችን በግዥ መለያ ቁጥር 01/2017 ማለትም፦
- ሎት 01 ቋሚ ዕቃ፣
- ሎት 02 የደንብ ልብስ፣
- ሎት 03 አላቂ የጽዳት እቃዎች፣
- ሎት 4 አላቂ የቢሮ እቃዎች፣
- ሎት 05 አላቂ የትምህርት ዕቃዎች፣
- ሎት 06 ለተለያዩ መሳሪያዎች እና መፃህፍት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ብር
- ሎት 01 የጨረታ ማስከበሪያ 20,420.00 (ሃያ ሺ አራት መቶ ሃያ)
- ሎት 02 የጨረታ መስከበሪያ ብር 30,002.40 (ሰላሳ ሺ ሁለት ከ40/00)
- ሎት 03 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 31,542.70 (ሰላሳ አንድ ሺ አምስት መቶ አርባ ሁለት ከ70/100)
- ሎት 04 የጨረታ ማስከበሪያ 8003.72 (ስምንት ሺ ሶስት ከ72/00)
- ሎት 05 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 34,650.54 (ሰላሳ አራት ሺ ስድስት መቶ ሃምሳ ከ54/00)
- ሎት 06 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 2000.00 (ሁለት ሺ) በባንክ በተረጋገጠ ሰነድ ሲፒኦ(CPO) ከጨረታው ሰነድ ጋር በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል በዚህም መሰረት፡-
- በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 150.00 ( አንድ መቶ ሃምሳ) ብቻ በመክፈል ሰነዱን ከአዲስ አምባ ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 05 ቀርበው መግዛት ይችላል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ አየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አምባ ት/ቤት ፋይናንስ ክፍል ጨረታው ይከፈታል።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በትምህርት ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 05 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎት 01፤ ሎት 02፣ ሎት 03 ሎት 04፣ ሎት 05፣ ሎት 06 ናሙና መቅረብ አለባቸው ሎት 01 በትምህርት ቤቱ ፍላጎት መግለጫ መሰረት ብቻ ይሆናል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
- የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው አዲስ አምባ አፀደ ህፃናት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ትምህርት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አድራሻ፡-ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 09 አዲስ ሰፈር ድልድይ ወደ ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን በሚወስደው መንገድ 200ሜትር ገባ ብሎ አዲስ ሰፈር ጣና ገበያ ማእከል ፊት ለፊት
ስልክ 011-442-0441 ወይም 011-470-7017
ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 09 አዲስ አምባ አፀደ ህፃናትና የመ/ደ/ት/ቤት
cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Education and Training cttx, cttx Electrical, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx House Furniture cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Materials cttx, cttx Office Furniture cttx, cttx Office Machines and Accessories cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Stationery cttx, cttx Textile, Electromechanical and Electronics cttx, Garment and Leather cttx