Your cart is currently empty!
በማ/ኢ/ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽሕፈት ቤት በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ቋሚ እና አላቂ የቢሮ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 23, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ጌ/ወ/ፋ/ግ/ጨ/ቁ/01/2018
በማ/ኢ/ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽሕፈት ቤት በ2018 በጀት ዓመት በተፈቀደው መደበኛና ካፒታል በጀት በወረዳችን የሚገኙ አጠቃላይ ሴክተር መ/ቤቶች እና የቋንጤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የተለያዩ ቋሚ እና አላቂ የቢሮ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል በመሆኑም ወረዳው የሚፈልጋቸው እቃዎች እንደሚከተለው በሎት ተከፋፍለው ቀርበዋል።
- ሎት 1 ስቴሽነሪ
- ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ
- ሎት 3 ጀነሬተር
- ሎት 4 የጽዳት እቃዎች
- ሎት 5 የደንብ ልብሶች
- ሎት 6 ሞተር ሳይክል ጎማና ኮመነዳሪዎች
- ሎት 7 ሞተር ሳይክሎች
- ሎት 8 የመኪና ጎማዎች
- ሎት 9 የፈርኒቸር እቃዎች
- ሎት 10 ህንጻ መሳሪያዎች
- ሎት 11 የውሃ እቃዎች ሲሆኑ ይህ የጨረታ ገዥ ተግባራዊ የሚሆነው በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ ባወጣው መደበኛ የጨረታ ሰነድ መሰረት ሆኖ የጨረታው ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በሙሉ የምታሟሉ ማንኛውም ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ ሲሆን፤
1 የጨረታ መወዳደሪያ ሃሳብ አቅራቢዎች የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር በጣት አሻራ ላይ የተመሰረተ እና የተረጋገጠ መረጃ ማቅረብ አለባቸው።
2 ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የተሰጠ ማስረጃና የታደሰ ንግድ ፈቃድ በሚወዳደሩበት ዘርፍ(ሎት) ጋር አንድ የሆነ ማቅረብ አለባቸው።
3. ተጫራቾች በእቃ አቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት በኦን ላይን ብቻ የተመዘገቡ እና ስለ መመዝገባቸው የሚገልጽ መረጃ /e_GP/ Electronic Government procurement/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. በበጀት አመቱ ከግብር ነጻ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ (የምስክር ወረቀት) ማቅረብ የምትችሉ (Tax Clearance)
5. በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
6. አሸናፊ ተጫራች ለግዥ ፈጻሚ የሚሰጠው ደረሰኝ የእጅ በእጅ ሽያጭ ደረሰኝ ከሆነ የንግድ ፈቃድ ባወጡበት ቦታ የገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ማህተም በጀርባው ሊኖረው ይገባል አለበለዚያ የእጅ በእጅ ሽያጭ ደረሰኝ ተቀባይነት የለውም።
7. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆኑ ለወደፊትም በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፉ በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያቸው ውርስ ይሆናል።
8. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ የዕቃ ብራንድ፣ የስሪት ዘመን፣ ሞዴል የተመረተበት ሀገር እና ሌሎች ስለ ዕቃው መጠቀስ ያለበትን ነገር መግለፅ አለባቸው።
9. እያንዳንዱ ተወዳዳሪ የእቃዎች ዋጋ ሲሞላ ቫት ጨምሮ መሆን አለበት ካልጨመሩ እንደ ጨመሩ ታሳቢ ይደረጋል።
10. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይንም ከጨረታ ራስን ማግለል አይቻለም።
11. በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚገዙትን የጨረታ ሰነድ ጠቀሰው በማመለከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ህጋዊ ውክልና ይዘው መቅረብ አለባቸው።
12. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በመግቢያ ከተገለጹት ከሎት 1-11 በተዘረዘሩ የቋሚ እና አላቂ እቃዎች ሎት 3 እና 4 ብር 7000 /ሰባት ሺህ ብር/ የተቀሩት ሎቶች እያንዳንዳቸው 10,000 /አስር ሺህ/ ብር ለፋይናንስ ጽ/ቤት CPO ሲፒኦ (በካሽ) ወይም ከመድን ድርጅቶች የሚቀርብ ዋስትና በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረት ለ90 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ቢድ ቦንድ በጌታ ወረዳ ፋይናንስ ስም እውቅና ባለው ባንክ ህጋዊ ሲፒኦ ማሰራት አለባቸው ለቋንጤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከሎት1-5 እና ሎት 9 ለተዘረዘሩት እቃዎች በእያንዳንዱ ሎት 3000 /ሶስት ሺህ/ ብር ሲፒኦ ወይም በካሽ በቋንጤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስም በማሰራት ማስያዝ አለባቸው።
13. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ በግልጽ ጽሁፍ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን አለበት።
14. ተጫራቾች በአንድ እናት ፖስታ የእያንዳንዱ ሎት ሲፒኦ በማካተት በጥንቃቄ ታሽጎ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ (ቅጂ) ሰነድ በድርጅቱ ባለስልጣን የተፈረመበት እና በእያንዳንዱ ገጽ ማህተም የተደረገበት ሆኖ እስከ ጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 በመምጣት ለፋይናንስ እና ለቋንጤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ብሎ በመለየት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን የሚመለከተው አካል በማሳወቅ በሳጥኑ መጨመር አለባቸው።
15. በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች የስራ ዝርዝር የያዘ ሰነድ ጨረታው ከታወጀበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛ ቀን 6፡00 ሰዓት ድረስ ጌታ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 በመምጣት የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት መውሰድ ይቻላል።
16. የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛው አስራ ስድስተኛው ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ ወይም እሑድ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን 8፡00 ሰዓት በጨረታው ኮሚቴ ታሽጎ በዛው እለት 8፡30 ተጫራቾች ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ባይገኙም ይከፈታል።
17. መ/ቤታችን የሚፈልጋቸው ጥራታቸው የጠበቁ የተለያዩ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ አላቂ እና ቋሚ እቃዎች ሲሆኑ ግዢ የምንፈጽምባቸው እቃዎች የምንረከበው በጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት መጋዘን እና በቋንጤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል መጋዘን ይሆናል።
18. አሸናፊ ከተለየ በውል ከተገባ በኋላ ግዢ የምንፈጽምባቸው እቃዎች መረከቢያ ጊዜ ግዢ ከታዘዘበት ቀን ጀምሮ ባሉ 25 ቀናት ውስጥ ይሆናል።
19. በግዥ ፈጻሚው አካል አሸናፊው ከተለየ በኋላ በሚገዛቸው ጥራታቸው የጠበቁ የተለያዩ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ አላቂ እና ቋሚ እቃዎች 20 ፐርሰንት የመቀነስ ወይም የመጨመር መብት ይኖረዋል።
20. የቀረበው የመወዳደሪያ ሃሳብ ዋጋ ጨረታው ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት።
21. በሁሉም ዘርፍ የሚወዳደሩ ተወዳዳሪዎች ለእቃዎቹ ናሙና ሳምፕል ሲጠየቁ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
22. በጨረታ ማስታወቂያና በጨረታ ሰነዱ መሃከል ልዩነት ከተፈጠረ የጨረታ ሰነዱ የበላይነት ይኖረዋል።
23. ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ላይ ማብራሪያ ወይም ማሻሻያ ጥያቄ ለግዥ ፈጻሚ አካል ማቅረብ የሚችሉት ጨረታው ከመክፈቻ 5 ቀናት በፊት በጽሁፍ መሆን አለበት።
24. ተጫራቾች የጨረታው የመወዳደሪያ ሀሳብ ማቅረቢያ ቋንቋው በአማርኛ በእንግሊዝኛ ነው።
- ማሳሰቢያ 1፡- ግዢ ፈጻሚው አካል ጨረታውን በሙሉ/ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል።
- 2. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱን ከተረጋገጠ በ7ኛው ቀን 1% ባሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ ያውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት።
ተጨማሪ መረጃ፡- 09 67 44 13 04/ 09 21 38 54 94/ 09 13 20 57 60
አዲስ አበባ ሰነድ የሂሳበ ስልክ ቁጥር 09 73 75 72 44/ 09 09 06 76 02/ 09 61 17 81 10/ 09 25 83 81 93
በማ/ኢ/ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽሕፈት ቤት