በጂማ ዞን የሸቤ ሶንቦ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት የጽህፈት መሳሪያ ና አላቂ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ፈርኒቸር፣ ሞተር-ሳይክል፣ ጀነሬተር፣ የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማ እና የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 23, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

በጂማ ዞን የሸቤ ሶንቦ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የእቃ አይነቶች በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡-

  1. የጽህፈት መሳሪያ ና አላቂ ዕቃዎች
  2. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
  3. ፈርኒቸር
  4. ሞተር-ሳይክል
  5. ጀነሬተር
  6. የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማ
  7. የደንብ ልብስ

ስለዚህ በዚህ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ፍቃድ ያሳደሱ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃቸውን ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/እና TIN No ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ሰርተፍኬት ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
  3. ተጫራቹ T.O. T ተመዝጋቢ ከሆነ ማስረጃውን ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  4. ተጫራቾች በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ለእያንዳንዱ የዕቃ ዓይነት ብር 5000 ህጋዊነቱ ከተረጋገጠ ባንክ በ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ከሸቤ ሶንቦ ወረዳ ገቢዎች ባለስልጣን ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 100 በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ በ15 የስራ ቀናት ውስጥ መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች አስፈላጊውን ሰነድ በሙሉ ፎቶ ኮፒውን በአንድ ፖስታ ውስጥ ከተው ኦሪጅናሉን ደግሞ በሌላ አንድ ፖስታ ውስጥ ከተው ፖስታዎቹን በሰም አሽገው ላዩ ላይ ፈርመውና ማህተም አድርገ ውበት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 15ኛው ቀን መጨረሻ ድረስ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
  8. ጨረታው የሚከፈተው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወጥቶ በ16ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች(ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት በመስሪያቤታችን የግዥ ከፍል (ቢሮ ቁጥር 3 ) በግልጽ ይከፈታል፡፡
  9. አሸናፊ ሆኖ የተገኘ ተወዳዳሪ የሚታዘዘውን ዕቃ በሙሉ ወጪውን ችሎ እስከ መስሪያቤታችን ድረስ የሚያቀርብ ይሆናል፡
  10. መስሪያቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር 047-118-0256

የሸቤ ሶጓቦ ወረዳ ገ/ ጽ/ቤት