Your cart is currently empty!
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ትምህርት ጽ/ቤት ፊታ/ሀ/ጊ ቁ. ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 23, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2018
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ትምህርት ጽ/ቤት ፊታ/ሀ/ጊ ቁ. ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል፡፡
- ሎት-1 አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች
- ሎት-2 የጽዳት ዕቃዎች
- ሎት-3 የደንብ ልብስ
- ሎት-4 አላቂ የህክምና እቃዎች ፣ የላቦራቶሪ እቃዎች
- ሎት-5 የተለያዩ ለጥገና የሚውሉ እቃዎች
- ሎት-6 ቋሚ መገልገያ እቃዎች እና መሣሪያዎች
- ሎት-7 የኮምፒውተር ጥገና ፎቶ ኮፒ ጥገና፣ ማባዣ ጥገና እንዲሁም የተለያዩ ጥገና ስራዎች
ከላይ በተዘረዘሩት ሎቶች መሰረት፡-
ሎት |
የእቃው/የስራው አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን |
አጠቃላይ በጀቱ የተወሰደው ብዜት |
1 |
አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች፣ |
6,000 |
0.5 |
2 |
የጽዳት ዕቃዎች |
6,000 |
0.7 |
3 |
የደንብ ልብስ |
6,000 |
0.9 |
4 |
አላቂ የህክምና እቃዎች ፣ የላብራቶሪ እቃዎች |
3,500 |
0.5 |
5 |
የተለያዩ ለጥገና የሚውሉ እቃዎች |
3,500 |
0.5 |
6 |
ቋሚ መገልገያ እቃዎች እና መሣሪያዎች |
3,500 |
0.7 |
7 |
የኮምፒውተር ጥገና፣ ፎቶ ኮፒ ጥገና፣ ማባዣ ጥገና እንዲሁም የተለያዩ ሥራዎች |
3,500 |
0.5 |
1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ
2. የአቅራቢዎች የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የቫት ተመዝጋቢ የሆነ
3. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከቀኑ 2፡30-11፡30 ሰዓት ድረስ የማይመለስ 100.00 ብር /አንድ መቶ ብር / በመክፈል ከግዥ አስተዳደር ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት በሰንጠረዡ ሥር በተቀመጠው ዝርዝር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በማሰራት ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፤ ተወዳዳሪዎች ማስረጃቸውንና የእቃዎቹን በአራት ኤንቨሎፕ ፋይናንሻል ኦርጅናል፣ ፋይናንሻል ኮፒ (ቅጂ)፣ ቴክኒካል ኦርጅናል እና ቴክኒካል ኮፒ (ቅጂ) ብሎ በመለየት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
5. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከቀረበው አጭር መግለጫ /specification/ ውጭ በመሰረዝ ወይም በማሻሻል ማቅረብ እና በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት አይፈቀድም።
6. ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ የውል ማስከበሪያ (CPO) 10% ያሲዛ
7. የጨረታው ሳጥን በ10ኛው ቀን አብቅቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ4፡30 ሰዓት በት/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን የሚከፈትበት ካላንደር የሚዘጋው ቅዳሜ እና እሁድ ወይም ሀገር አቀፍ ክብረ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል።
8.ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ሎቶች ላይ ናሙናዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው።
9. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃ በራሱ የትራንስፖርት ወጪ መ/ቤቱ ድረስ የማቅረብና የማስረከብ ግዴታ አለበት፡
10. ት/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መ/ቤቱ የተጠበቀ ነው።
11. ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ ሙበቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ፊታ/ሀ/ጊ የመ/ደ/ት/ቤት ጥቁር አባይ ጫማ ፋብሪካ ወረድ ብሎ ወደ አዲስ ሰፈር በሚወስደው መንገድ 100 ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል።
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 011 273-0565 ወይም 011-270 1707
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ት/ት ጽ/ቤት ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ቁ 1 የመ/ደ/ት/ቤት