Your cart is currently empty!
የገላን ጉዳ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ጽህፈት መሳሪያዎች፣ ጽዳት እቃዎች እና ሌሎች አላቂ እቃዎች፣ የመኪና ጎማዎችን፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 23, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የገላን ጉዳ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለክፍለ ከተማው ሴክተር መስሪያ ቤቶች እና ለማዘጋጀ ቤት አገልግሎት የሚውሉ፤-
- ሎት 1 ጽህፈት መሳሪያዎች፣ ጽዳት እቃዎች እና ሌሎች አላቂ እቃዎች
- ሎት 2 የመኪና ጎማዎችን፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ትችላላችሁ።
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የታደሰ እንዲሁም የሚፈለግባቸውን ግብር አጠናቀው ስለመክፈላቸው በቂ ማስረጃ (ክሊራንስ) ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ወደ ስንቄ አካውንት ቁጥር 1064724141216 ገቢ በማድረግ ከገቢዎች ባለስልጣን በተወከለው ሠራተኛ አማካኝነት ወደ ደረሰኝ በማስቀየር ዘወትር በስራ ሰዓት በመክፈል መግዛት ይችላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት በተዘጋጀው ሰነድ ብር 30,000.00 (ሠላሳ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት CPO ብቻ በገላን ጉዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም አዘጋጅተው ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ሰነዱን ከገዙ በኋላ የሚሸጡበትን ዋጋ በመጥቀስ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ በተባለው ቀን ውስጥ ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችዋል።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፤ እንዲሁም ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ቫትን (15%) ያካተተ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው ቦታ (ዕቃ ግምጃ ቤት) ድረስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባችዋል።
- ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች ገቢ የሚሆነው አስፈላጊውን ጥራት ማሟላቱ በባለሙያ እና ጥራት አጣሪ ኮሚቴ ሲረጋገጥ ብቻ ይሆናል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት እቃ ከስቶክ ወይም ከራሳቸው ስቶር መሆን ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራት ቀናት የሚሸጥ ሆኖ በ16ኛው ቀን፣ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተጠቀሰው ቀን 4፡30 የሚከፈት ይሆናል።
- ከላይ የተገለጸው የመክፈቻ ቀን በዓል ወይንም የሰንበት ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በቀጣዩ የስራ ቀን ይሆናል።
- አድራሻ ገላን ጉዳ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት በተለምዶ አለምገና (ኬንቴሪ ) ዋንጋር ሕንጻ 3ፎቅ ነው።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የገላን ጉዳ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Computer and Accessories cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Spare Parts and Car Decoration Materials cttx, Electromechanical and Electronics cttx