Your cart is currently empty!
በቄለም ወለጋ ዞን የየማሎጊ ወለል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 ዓ/ም በጀት በወረዳው ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሚውል ቋሚ እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን እንዲሁም የደንብ ልብስ በጨረታ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 23, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የተጫራቾች ደንብ እና መምሪያ /Bidders Instruction/
በቄለም ወለጋ ዞን የየማሎጊ ወለል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 ዓ/ም በጀት በወረዳው ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሚውል ቋሚ እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን እንዲሁም የደንብ ልብስ በጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት ተጫራቾች፡-
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የ2017 የመንግስት ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው.
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ መረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- በ/ገ/ኢ/ት/ሚኒስቴር ባቅራቢዎች የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታው ተካፋይ ለመሆን የሚፈልጉት ዕቃ በምን በምን አይነት እቃዎች ላይ መሆኑን ለይተው መግለፅ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፁትን ማንኛውንም ሁኔታዎችን መለወጥ ወይም ማሻሻል ጨረታውን ትቼዋለሁ ማለት አይቻልም።
- መስሪያ ቤቱ የሚገዛውን እቃዎች ብዛት እንደአስፈላጊነታቸው በሙሉ ወይም በከፊል ማዘዝ ይችላል።
- የሚቀርቡት እቃዎች በተሰጠው እስፔስፊኬሽን ካልቀረቡና ማንኛውም አይነት ስህተት ቢፈፀም ሃላፊነቱ የአቅራቢው ይሆናል።
- ጨረታው የሚካሄደው የድርጅቱን የገበያ ጥናት ማዕከል የሚደረግ ሲሆን ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃዎች አይነት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራቹ ያንዱን ዕቃ ዋጋ በቁጥርና በፊደል መፃፍ አለበት። በቁጥርና በፊደል በተፃፈ መካከል ልዩነት ቢኖር ፊደል የተጻፈው ይወሰዳል።
- አቅራቢው ድርጅት እቃዎችን ቄለም ወለጋ ዞን በየማሎጊ ወለል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መጋዝን ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ላሸነፉባቸው እቃዎች ከመስሪያቤቱ ጋር ውል መግባት አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 (አሥር ሺህ) ብር ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል።
- አሸናፊዎች በሚገቡት ውል መሰረት ለመፈጸም ለውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ ላይ 10% በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ለውል ማስከበሪያ የተያዘ ሲፒኦ በውሉ መሰረት እስኪፈጸም ተይዞ ይቆያል።
- ከዚህ በላይ በተገለጸው መሰረት ተጫራቾች ውሉን በአግባቡ ሳይፈጽሙ ቢቀሩ ለውል ስምምነት ያስያዙት ገንዘብ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ይሆናል።
- ተጫራቾች በሰነዳቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን ገልጸው መፈረም አለባቸው።
- የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ የሚታይ መሆን አለበት።
- ከተጠየቀው ብዛት አሳንሶ ማቅረብ አይቻልም።
- ተጫራቾች ከጨረታው መክፈቻ እለት ጀምሮ ያቀረቡት ዋጋ የሚቆይበት ጊዜ አጠናቀው /validity date/እቃውን የሚያስገቡበትን ቀን መግለፅ አለባቸው።
- አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- ተጫራቾች መሸነፋቸው እንደተረጋገጠ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያው ይመለስላቸዋል።
- ተጫራቾች ከሽያጭ በኋላ የሚሰጡት አገልግሎት/aftersales service) መግለፅ ይኖርባቸዋል።
- ዋጋው መሞላት ያለበት መ/ቤቱ ባዘጋጀው ሰነድ ላይ ብቻ ነው።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ 21 ተከታታይ ቀናቶች አየር ላይ ውሎ በዚሁ ቀን በ11:00 ሰዓት ተዘግቶ በማግስቱ ከጠዋቱ 2፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- በዚህ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የጨረታ ሰነድ በማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) ከየማሎጊ ወለል ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት መግዛት ይችላል።
- ተጫራቾች የቴክኒክና የዋጋ ፖስታ ለየብቻ ወይም በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለባቸው.
- ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበው ዋጋ ቫትን ጨምሮ ማቅረብ አለበት። ወይም የሚያቀርበው ዋጋው ከቫት ጋር መሆን አለበት።
- ማንኛውም ተጫራች መ/ቤቱ የፈለጋቸውን ዕቃ ያንዱን ዋጋ መሙላት አለበት። ሞልቶ ካልተገኘ የሌላ ተጫራች ትልቁ ዋጋ ይደመርበታል። ጨረታው የሚገመገመው የመ/ቤቱ የገበያ ጥናትን ማዕከል ያደረገ ሲሆን ከገበያ ጥናቱ 10 ከፍ ያለ ዋጋ ወይንም ዝቅ ያለ ዋጋ ውድቅ ይደረግና የገበያው የዕቃው የተጠና ዋጋ ይደመርበታል።
- በቄለም ወለጋ ዞን የየማሎጊወለል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ተጆ ከተማ የጨረታው ሰነድ ስለሚገኝ መጥቶ መግዛት ይቻላል።
- ማሳሰቢያ፡- የመ/ቤታችን የግዥ መጠን በ20/% መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል።
- መ/ቤታችን የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።
ለተጨማሪ መረጃ
አድራሻ፡- ቄለምወለጋ ዞን የማሎጊ ወለል ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ተጆ
ስልክ ቁጥር፡- 09 10 31 08 20 / 09 17 36 90 84
በቄለም ወለጋ ዞን የየማሎጊ ወለል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Computer and Accessories cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Shoes and Other Leather Products cttx, cttx Textile, Electromechanical and Electronics cttx, Garment and Leather cttx, Garments and Uniforms cttx