በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ የፉሪ ከፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለመስሪያ ቤቱ የሚያገለግሉ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ ቋሚና አላቂ የቢሮ ውስጥ እቃዎችን፣ ህትመቶች፤ የሠራተኛ የደንብ ልብሶች እና የዳኞች የችሎት ልብስ፤ ኤሌክትሮኒክስ፤ ፈርኒቸሮች፤ መጋረጃ እና የቢሮ ምንጣፎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 05, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የግዢ የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ የፉሪ ከፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት 2018 በጀት ዓመት ለመስሪያ ቤቱ የሚያገለግሉ በሎት አንድ (1) የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች ቋሚና አላቂ የቢሮ ውስጥ እቃዎችን፣ ህትመቶች የሠራተኛ የደንብ ልብሶች እና የዳኞች የችሎት ልብስ ኤሌክትሮኒክስ፤ ፈርኒቸሮች፤ መጋረጃ እና የቢሮ ምንጣፎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በዘርፉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላው የንግድ ድርጅት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ወደ ስንቄ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1064669901216 ገቢ በማድረግ (በመክፈል) ደረሰኙን በመያዝ ከፉሪ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የፋይናንስ እና ንብረት ግዥ አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 02 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡

1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የታደሰ እንዲሁም የሚፈለግባቸውን ግብር አጠናቀው ስለመክፈላቸው በቂ ማስረጃ (ክሊራንስ) ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከባንክ የተረጋገጠ CPO ብቻ 10,000.00 (አስር ብር) በፉሪ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በማሰራት ከሠነዱ ጋር በማሸግ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

3. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ ስም እና አድራሻ በማድረግ በድርጅቱ ስልጣን ባለው አካል ማህተም እና ፊርማ በማረጋገጥ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ በፉሪ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የፋይናንስ እና ንብረት ግዥ አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 02 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

4. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት (VAT 15%) ተመዝጋቢ የግብር ከፋይነት (TIN NO) ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል እንዲሁም ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ (ቫትን 15% ) ያካተተ መሆን አለበት፡፡

5. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው ቦታ ድረስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

6. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች ገቢ የሚሆነው አስፈላጊውን ጥራት ማሟላቱ በባለሙያ እና ጥራት አጣሪ ኮሚቴ ሲረጋገጥ ብቻ ይሆናል፡፡

7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት እቃ ከስቶከ ወይም ከራሳቸው እስቶር ሆኖ እቃዎቹ ጥራቱን የጠበቁ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

8. ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

9. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት የሚሸጥ ሆኖ 16 (አስራ ስድስት) ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ተዘግቶ በተጠቀሰው ቀን 430 የሚከፈት ይሆናል፡ እለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡

10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ወይም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡በፉሪ ፍለ ከተማ ወለቴ ኖክ አደባባይ ሰበታ መንገድ 100 ሜትር አለፍ ብሎ ጂኤም ፈርኒቸር ሕንፃ ላይ።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 011-380 5086/ 011-380 5230

በሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፉሪ ክፍ ከተማ ወረዳ /ቤት