በየካ ክ/ከተማ የካ ጤና ጣቢያ በ2018 በጀት ዓመት መገልገያ የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ተጫራቾችን መጋበዝ ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 05, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

1 ዙር ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በየካ /ከተማ የካ ጤና ጣቢያ 2018 በጀት ዓመት መገልገያ የሚውሉ

  • የደንብ ልብስ፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ ህትመት፣ የፅዳት እቃዎች፣
  • የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የጥገና ዕቃዎች፣ የቢሮ ዕቃዎች፤ ኮምፒውተርና ተዛማጅ ዕቃዎች፣
  • ምግቦች፣ የእስፖርት እቃዎች፣ ቋሚ አላቂ እቃዎች ግዢ እና የህክምና እቃዎች ጥገና፣
  • የጥገና ስራዎች እንዲሁም የሚወገዱ መድሀኒቶችና ሪኤጀንቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ተጫራቾችን መጋበዝ ይፈልጋል።

በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል።

1. ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸውና የታደሰ የንግድ ፍቃድ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

2. ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑ አለባቸው።

4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በየሎት

  • 1, ለፅዳትእቃዎች -5000ብር
  • 2, ለደንብ ልብስ– 5000 ብር
  • 3 ለፅህፈት እቃዎች -5000 ብር
  • 4 ለቢሮ እቃዎች– 5000 ብር
  • 5 ለኮምፒውተር ተዛማጅ እቃዎች-7500ብር
  • 6 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች– 10000ብር
  • 7 ህትመት ስራዎች– 4500 ብር
  • 8 ደንብ ልብስ ስፌት -1000ብር
  • 9 ጥገና እቃዎች– 6500 ብር
  • 10 ጥገና ስራዎች -4500 ብር
  • 11 የህክምና እቃዎች ጥገና 1000 ብር
  • 12 የሚወገዱ መድሀኒቶችና ሪኤጀንቶች – 2000 ብር
  • 13 የእስፖርት እቃዎች– 1000 ብር
  • 14 ምግቦች 1000 ብር
  • 15 ቋሚ አላቂ እቃዎች-1000 ብር

በድርጅቱ ስም ሲፒኦ (CPO) በማዘጋጀት ማረጋገጫውን ከመወዳደሪያ ሰነዶቻችው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ በጥንቃቄ ሞልተው በመፈራረም እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋናውን እና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በየካ ጤና ጣቢያ 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ግዥ ቡድን በመገኘት ሰነዱን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

7. ጨረታው በ11ኛው ቀን 4 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 430 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

8. የጨረታውን ሰነድ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ካጋጠመ ተጫራቹ ስርዙ ጎን ፊርማውን ማስቀመጥ ይኖርበታል።

9. አሸናፊው ድርጅት ማሸነፉ በተገለፀለት 7 የስራ ቀናት ውስጥ የመደበኛ ውል ሰነድ መፈራረም ይኖርበታል።

10. አሸናፊው ድርጅት ከአሸነፈው ጠቅላላ ዋጋ ላይ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት።

11. ጤና ጣቢያው የአቅርቦት ዝርዝር (ስፔስፍኬሽን) በሚጠይቁ አቅርቦቶች ላይ ባወጣው መሰረት ተጫራቾች ካታሎግን ጨምሮ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

12. የጨረታም ሆነ የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ አሸነፋችሁም አላሸነፋችሁም 6ወር በፊት መውሰድ ይኖርባችዋል 6ወር በኋላ የሚወረስ መሆኑን እናሳውቃለን።

13. ጤና ጣቢያው የተሻለ መንገድ የሚያጋጥመው ከሆነ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡የካ ጤና ጣቢያ ሾላ ገበያ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት

ስልክ ቁጥር -011 893 29 82/011 667 42 37

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካ ክፍለ ከተማ ጤና /ቤት የየካ ጤና ጣቢያ