Your cart is currently empty!
የብልጽግና ፓርቲ ኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2018 የበጀት አመት የተለያዩ ለቢሮ ውስጥ አገልግሎት የሚውሉ ቋሚና አላቂ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 05, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ
የጨረታ ቁጥር ብ.ፓ.ኦ.ቅ/ጽ/ቤት/01/2018
የብልጽግና ፓርቲ ኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2018 የበጀት አመት የተለያዩ ለቢሮ ውስጥ አገልግሎት የሚውሉ ቋሚና አላቂ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎቱና አቅሙ ያላችሁ ድርጅቶች ከዚህ በታች በቀረቡት መስፈርቶች መሰረት የጨረታ ሰነድ ከፓርቲው ግዢና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ከፍል 1ኛ ፎቅ ቁ 106 በመግዛት መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡
ተፈላጊ መስፈርቶች –
1. አግባብነት ያለውና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ ያላቸው፣
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
3. VAT ሰርተፍኬት ተመዝጋቢ የሆኑ፣
4. የገቢዎች ከሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣
5. የተጨማሪ እሴት ታከስና የግብር መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና CPO 2% በባንከ በተያዘ የከፍያ ትዕዛዝ ማስያዝ የሚችሉ፣
7. ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ከገዙበት ዕለት አንስቶ እስከ መስከረም 10/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ዘውትር በስራ ቀናት ኢ.አ ከመስቀል አደባባይ ወደ ጎተራ በሚወስደው መንገድ ከቶታል ማደያ አለፍ ብሎ ከሰንጆሴፍ ት/ቤት ፊትለፊት በሚገኛው የፓርቲው ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ማስገባት አለባቸው፡፡
8. ተጫራቹ የተዘጋጀውን የመወዳደሪያ ሰነድ በመሙላት በአንድ ኮፒ በማዘጋጀት መስከረም 12/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ3፡00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ለዚህው አላማ በተዘገጀው ሳጥን ውስጥ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ 4ኛ ፎቅ ቢ.ቁ 308 በማምጣት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
9. ጨረታው ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መስከረም 12/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚው ቀን በ4፡30 ሰዓት በፓርቲው አዳራሽ 4ኛ ፎቅ የሚከፈት ሲሆን ዘግይቶ የሚመጡ የመወዳደሪያ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
10. ተጫራቹ የአሸናፊነት ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ በሁለት የስራ ቀናት ውስጥ ውል ገብቶ የመልካም ሥራ አፈፃፀም 10% ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡
11. በውሉ መሰረት ዕቃውን የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡
12. ቅድመ ክፊያ የሚጠይቅ ከሆነ ከክፊያው ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ዋስትና ማቅረብ አስፈላጊ ይሆናል፡፡
13. ፓርቲው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ሥ.ቁ፦ +251 91 072 4345/+251 98 714 4447 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
የብልጽግና ፓርቲ ኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት