የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የፈርኒቸር ዕቃዎችን ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 04, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

.../ብግጨ /ዕግ/13/12/2017

  1. የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የፈርኒቸር ዕቃዎች ግዥ በጨረታ መለያ ቁጥር ...ብግጨ ዕግ/3/12/2017 ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
  2. ለኮርፖሬሽኑ አገልግሎት የሚያገለግል የፈርኒቸር ዕቃዎች ግዥ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ቴክኒካል ሰነዳቸውንና ዋጋቸውን በተለያዩ በታሸጉ ኤንቨሎፖች ማቅረብ አለባቸው።
  3. ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነሥርዓትና ይኸንኑ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በወጣው የመንግሥት የግዥ አዋጅ መሠረት ሲሆን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርበታል።
  4. የተሟላ የአማርኛ የጨረታ ሰነዶችን ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለገሀር በሚገኘው በተለምዶ የስነምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን ህንፃ 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 209 በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 209/212 ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ወይም ቀን 15/01/2018 ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00 (ሠላሳ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ቼክ ወይም ሲፒኦ በፌዴራል ቤቶች ኮፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው። ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፤ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 15/01/2018 ከጠዋቱ 400 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 415 ሰዓት የኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተደደር ዳይሬከተር 2 ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
  6. ኮርፖሬሽኑ በሚያወጣው ፕሮግራም መሠረት አሸናፊው ተጫራች የፈርኒቸር ዕቃዎች ቢሮ ግዥውን በኮርፖሬሽኑ ቅጥር ግቢ ያስረከባል።
  7. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-515-77-28 ወይም 011-553-95-35 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *