Your cart is currently empty!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ በ2018 በጀት ዓመት ለኤጀንሲው የሚያስፈልጉ የተለያዩ አላቂ ዕቃዎች፣ ደንብ ልብስ፣ ቋሚ ዕቃዎች፣ የኢቨንት ስራዎች እና የህትመት ስራዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 05, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ በ2018 በጀት ዓመት ለኤጀንሲው የሚያስፈልጉ የተለያዩ እቃዎች ሎት1 አላቂ ዕቃዎች፣ ሎት 2፡ ደንብ ልብስ፣ ሎት 3 ቋሚ ዕቃዎች እና ሎት 4 የኢቨንት ስራዎች፣ ሎት 5 የህትመት ስራዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች
1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑ ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው። በኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገበበት ማስረጃ ማያያዝ አለባቸው።
2. የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ፒያሳ ከጣይቱ ሆቴል ጀርባ ዋስትና የንግድ ማዕከል 5ኛ ፎቅ ከግዥ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ህጋዊ ሥልጣን ያለውን አካል ፊርማ በማኖር በሰም በታሸገ ማህተም ያረፈበት ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ10ኛው የሥራ ቀን 11፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ዋስትና የንግድ ማዕከል 5ኛ ፎቅ የግዥ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል። ነገር ግን 11 ኛው ቀን በዓል፣ ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል።
5. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ 2% Unconditional Bank Guaranty ወይም CPO ማስያዝ አለባቸው። እያንዳንዱ ተወዳዳሪ የቴክኒክና የፋይናንስ ሰነድ አንድ ኦርጂናል እና አንድ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
6. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ስስክ ቁጥር፡-011 533 6497
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ