Your cart is currently empty!
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ጫማ፣ የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የደንብ ልብስ፣ የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የተለያዩ ትጥቆች እና የምክር አገልግሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 05, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር አ/አ/ደ/ማ/ባ/እቃ/ግ/ጨ/02/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ እቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት ቁጥር |
የሚገዛው የእቃ ዓይነት |
ምርመራ |
1 |
የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ጫማ |
720,000.00 |
2 |
የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የደንብ ልብስ |
1,000,000.00 |
3 |
የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የተለያዩ ትጥቆች |
200,000.00 |
4 |
የምክር አገልግሎት |
14,000.00 |
በዚህ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመሪያዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡–
1, በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው የሚያረጋገጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣
4. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ቲን TIN ማቅረብ የሚችሉ፣
5. የአቅራቢነት ምዝገባ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ፣
6. ወታደራዊ ጫማ በማቅረብ ለ10 ዓመት እና ከዚያ በላይ ልምድ ያለው መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም የእራሱ ማምረቻ ፋብሪካ ያለው።
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ ከ2፡30-11፡00 ሰዓት ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 08/15 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
8. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒ እንዲሁም ፋይናሻል ኦርጅናልና ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለየብቻው በማቅረብ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ግዥና ንብረት አ/ጠ/አ/ዳይሬክቶሬት 9ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09/22 ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. የሚቀርበው ዋጋ ማቅረቢያ ፊርማና ማህተም ከሌለው ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ናሙና የተጠየቀባቸው እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው።
10. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡00 ሰዓት ይከፈታል።
11. ተጫራቾች በሚጫረቱበት እያንዳንዱ እቃ ጥራት በቴክኒክ ብቃታቸው ከተመረጡ በዋጋ የሚወዳደሩ ይሆናል።
12. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡት የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
13. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡– አ/አ አራዳ ክፍል ከተማ (ፒያሳ) ልዩ ስሙ እሪ በከንቱ ተብሎ በሚጠራው የኢትዮጵያ ስታቲስቲካል አገልግሎት ቢሮ አካባቢ እስጢፋኖስ መካሻ አማረ (EMA )ህንፃ 9ኛ ፎቅ፣ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 562 2343 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን