የቤት ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ


Melekite Dire(Sep 03, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

    በፍ/ባለመብት እነ

  1. /ሪት ሊና መሐመድ ሐሩን 
  2. / ቤተልሔም መሐመድ ሐሩን
  3. አቶ አቤል መሐመድ ሐሩን እና 

   በፍ/ባለ እዳ እነ

  1. / ደብሮ በከር
  2. አቶ ካሊድ መሐመድ 
  3. / ፋይዛ መሐመድ  
  4. አቶ አህመድ መሐመድ      
  5. / አዚዛ መሐመድ 
  6. / አልፊያ መሐመድ 
  7. አቶ አብዱልናስር መሐመድ
  8. ወ/ ሔሌን መሐመድ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ጉዳይ በመዝገብ ቁጥር 105345 የተሰጠውን ውሣኔ ለማስፈፀም በድሬዳዋ ከተማ በቀበሌ 03 ክልል በሟች መሐመድ ሃሩን ዋሬ ስም በካርታ ቁጥር 224 የተመዘገበ ቤት የቤት ቁጥር 128 የሆነ ቤት መነሻ ግምቱ ብር 1,755,636.33/ አንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሃምሣ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ሰላሣ ስድስት ብር 33/100/ እንዲሸጥ ታዟል። በመሆኑም ጥቅምት 15 ቀን 2018 . በጨረታ አወዳድሮ በሐራጅ መሸጥ አስፈልጓል። ስለሆነም በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 300 እስከ 350 ድረስ ባለው ጊዜ የተጫራቾች ምዝገባ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው በተጠቀሰው ቀን እና ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ከጠዋቱ 400 እስከ 500 ባለው ጊዜ ይከናወናል። በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ ማንነታችሁን የሚይረጋግጥ መታወቂያ በመያዝ እና የጨረታው መነቫ ¼ ኛውን ወዲያው በሲፒኦ (CPO) በባንክ አስይዘው እንዲመዘገቡ በሲፒኦ (CPO) ያላስያዘ ተጫራች እንዳይመዘገብ በጥብቅ ታዟል። ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በመገኘት መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ያሸነፉበትን ገንዘብ ¼ኛውን ወዲያውኑ በሞዴል 85 በፍ/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል ማስይዝ አለባቸው። ቀሪውን ¾ኛ ገንዘብ ደግሞ ጨረታው በተካሄደ በ 15 ቀናት ውስጥ አጠናቀው ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።ይህ ባይሆን ቀድሞ የተያዘው ገንዘብ ለጨረታ የወጣው ወጪ ተቀንሶለት ቀሪው ለመንግስት ገቢ እንደሚሆን ሊገነዘቡ ይገባል።

የድሬዳዋ ምድብ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት 4ኛ ፍትሐብሔር ችሎት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *