Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ ትቅደም ቁ.1 ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 03, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2018ዓ.ም
የኢትዮጵያ ትቅደም ቁ.1 ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በመንግሥት መደበኛ በጀት በተገኘ ገንዘብ በቂ አቅራቢ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 የሠራተኛ ደንብ ልብስ
- ሎት 2 የሠራተኛ ደንብ ልብስ ስፌት
- ሎት 3 የቢሮ የጽሕፈት አላቂ እቃዎች
- ሎት 4 አላቂ የትምህርት እቃዎች
- ሎት 5 የህትመት ሥራዎች
- ሎት 6 / የህክምና አላቂ እቃዎች
- ሎት 7/ አላቂ የጽዳት እቃዎች
- ሎት 8/ ቋሚ ኤሌክትሮኒክስ
- ሎት 9/ ቋሚ ፈርኒቸር እቃዎች
- ሎት 10/ ፕላን ማሽነሪ ጥገና
- ሎት 11/ የተለያዩ ጥገና
- ሎት 12/ መጽሐፍት
በዚህ መሰረት ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች መሟላት አለባቸው።
- በሙያው ዘርፍ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል እና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ።
- በተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የዚህን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ በየሎት ብር 150.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቢሮ ቁጥር 9 መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ጨረታ ማስከበሪያ የሚያገለግል ለቋሚ እቃ በየሎት ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) እና ለሌሎች አላቂ እቃዎች በየሎት ብር 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር) በባንከ በተመሰከረለት ሲፒኦ ብቻ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት በሁሉም ሎቶች ሳምፕል ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ የሚያቀርቡትን ዋጋ በክፍል አራት ፤ ስድስት እና ዘጠኝ ላይ መሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋና እና ኮፒ በት/ቤቱ ፋይናንስና ግዢና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 9 በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት በየሎት የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በተናጠል በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርበታል።
- የጨረታ ሳጥኑ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ 9 ቁጥር ይከፈታል።
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት እና ወዛደር የት/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ዋጋው ፀንቶ የሚቆየው አሸናፊው ከተለየበት ቀን አንስቶ ለ60 ቀናት ይሆናል።
- በጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ በሚያመርቱት ምርት ከሆነ ሰነዱ በነጻ የሚወስዱ ይሆናል በማያመርቱት ምርት ላይ ሰነድ የሚጋዙ ይሆናል።
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች በአሸነፉበት የእቃ ርክክብ የሚደረግበት ሰዓት 2፡30 እስከ 6፡00 ቴክኒክ ኮሚቴዎች መኖራቸውን አረጋግጦ ማምጣት አለበት።
- አድራሻ፡– ልዩ ቦታ ከሰሜን ሆቴል ከፍ ብሎ ከዜና አገልግሎት በስተጀርባ ዶሮ ተራ
- በስልክ ቁጥር፦ 011 171 2200 እና 011 155 0724 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
- ማሳሰቢያ፡– በተጠየቁበት እቃ ሳንፕስ ያላቀረበ ነጋዴዎች ጨረታቸው ውድቅ ይሆናል።
አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የኢትዮጵያ ትቅደም ቁ.1 ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
cttx Advertising and Promotion cttx, cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Education and Training cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx Health Care, cttx Health Related Services and Materials cttx, cttx House Furniture cttx, cttx Materials cttx, cttx Medical Equipment and Supplies cttx, cttx Office Furniture cttx, cttx Pharmaceutical Products cttx, cttx Printed Advertising Materials cttx, cttx Promotional Items cttx, Electromechanical and Electronics cttx, Medical Industry cttx