Your cart is currently empty!
በአራዳ ክፍለ ከተማ የደጃ/በላይ ዘለቀ ቁ.1 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም የሚሆኑ የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 03, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2017
በአራዳ ክፍለ ከተማ የደጃ/በላይ ዘለቀ ቁ.1 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ2018 ዓ.ም የሚሆኑ የእስቴሽነሪ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች ፣ የስፖርት ትጥቅ/ ቱታ ጫማ/ ጫማ የአገር ውስጥ ምርት እና የስፖርት እቃዎች ፣ የኬሚካል ዕቃዎች፣ የቋሚ ዕቃ፣ የቢሮ ወንበር ጠረጴዛ፣ የፋይል ማስቀመጫ ሼልፍ፣ ሎከር የብረት፣ አልጋ ፤የማስታወቂያ መለጠፊያ ቦርድ፣ ላፕቶፕ ፣ ሀርድዲስክ ፣ ኮንፒውተር ፣ ፕሪንተር ፣ ፕሮጀክተር ፣ ፎቶካሜራ ፣የኢንተርኔት ሃርድ ዲስክ፣ ስካነር ፣ እስፒከር ፣ ቴሌቨዥን ፣ ዋይርለስ ማይክራፎን ፣ አይስርከርድ ጠንካራ፣ፓወር ሰፕላይ ፣ ጀነሬተር መካከለኛ ፣ ስታፕላይዘር፣ የውሃ ማጣሪያ ለመግዛት የመምህራን ጋውን ፤የጽዳትና ጥበቃ የደንብ ልብስ ግዥና ስፌት ለማሰፋት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።
1. በሙያው ዘርፍ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል እና የዘመኑን ግብር ለመከፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
2. በገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡበት የምዘገባ የምስክርነት ወረቀት የሚያቀርቡ
3. በተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የዚህን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በፋይናንስ ቢሮ መውስድ ይችላሉ።
5. በተጠየቁበት ዕቃ ናሙና ያላቀረቡ ነጋዴዎች ጨረታቸው ውድቅ ይሆናል።
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከጠቅላላው ዋጋ 2% በት/ቤቱ ስም ሲፒኦ በማስያዝ ከመወዳደሪያ ሰነድ ጋር በፋይናንስ ክፍል ቢሮ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 የስራ ቀናት ውስጥ የሚያቀርቡትን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋና እና ኮፒ በት/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
8. የጨረታ ሳጥኑ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል።
9. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በመሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት አና ሰራተኛ የት/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
11. ተጫራቾች አሸንፈው ውል በሚፈጽሙ ጊዜ ያሸነፉበትን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው።
አድራሻ፡– ከየካቲት 12 ሆስፒታል ጀርባ ከናዝሪት ት/ቤት ከፍ ብሎ
በስልክ ቁጥር-0111 730 598 እና 011-1-56-52-46 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ት/ጽ/ቤት የደጃ/በላይ ዘለቀ ቁ.1 2ኛ ደረጃ ትቤት