Your cart is currently empty!
የለገ ጣፎ ለገዳዲ ክ/ከ ወረዳ ፍርድ ቤት የተለየዩ የደንብ ልብስ፣ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች (ፈርኒቸር)፣ የኤሌክትሮኒከስ እቃዎችና የመሳሰሉት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 03, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግዢ ጨረታ ቁጥር 001/2018 ዓ/ም መመሪያ
የለገ ጣፎ ለገዳዲ ክ/ከ ወረዳ ፍርድ ቤት በ2018 የበጀት አመት
- የተለየዩ የደንብ ልብስ፣
- የጽህፈት መሣሪያዎች፣
- የጽዳት ዕቃዎች፣
- ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች (ፈርኒቸር)፣
- የኤሌክትሮኒከስ እቃዎችና የመሳሰሉት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት
ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተገለፁትን መመሪያ መሠረት ተጫራቾች ይህንን የጨረታ መመሪያ አክብረው እንዲካፈሉ እናሳውቃለን።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል ሀዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፋሉ፤የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እና የቲን ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በሌላም በሚመለከታቸው ፈቃድ ሰጪ አካላት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታ መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለው ማለት አይችልም።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበርያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር ብቻ ) በባንክ በተመሰከረለት (CPO) ማስያዝ አለባቸው።
- አሸናፊዎች በሚገቡት ውል መሰረት ለመፈጸም ለውል ማስከበሪያ ያሸነፉትን ጠቅላለ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) ወይም (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10፡30 ሰዓት ድረስ በለገ ጣፎ ለገ ዳዲ ክ/ከ/ ወረዳ ፍርድ ቤት ፋይናንስ ቢሮ በመቅረብ የማይመለስ 200.0 /ሁለት መቶ ብር / ብቻ ለለገ ጣፎ ለገ ዳዲ ክ/ከ ወረዳ ፍርድ ቤት በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣ ጀምሮ እስከ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ከቀኑ በ6፡30 ሰዓት በመስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ በመቅረብ ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በዚሁ ዕለት ኵኑ 6፡30 ታሽጎ በ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ለለገ ጣፎ ለገዳዲ ክ/ከ ወረዳ ፍርድ ቤት ፋይናንስ ቢሮ ይከፈታል። ሆኖም ባለቤቱ ወይም ህጋዊ ወኪሉ ባልተገኙበትም ይክፈታል፡፡ ነገር ግን ህጋዊ ውክልና የሌለው ሰው ምንም ዓይነት ጥያቄ ወይም ሀሳብ ማቅረብ አይችልም።
- የጨረታ ሰነዱ በሰዓቱ በጨረታ ሣጥን ውስጥ ካልገባ ተቀባይነት የለውም።
- የጨረታው ሠነድ ኦርጅናልና ኮፒው ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማግባት አለበት።
- የጥቃቅንና አነስተኛ ማይከ ኢንተርፕራይዝ ለውድድር የሚቀርቡት የዘመኑን ሂሳብ ኦዲት አስደርገው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- የጥቃቅንና አነስተኛ ማይክሮ ኢንተርፕራይዝ የጨረታ ማስከበሪ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር ብቻ በባንክ በተመሰከረለት (CPO) ማስያዝ አለባቸው፡፡ ሆኖም ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማሉ።
- ፍርድ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ 0116682321/0910922604/0933723568
የለገ ጣፎ ለገዳዲ ክ/ከ/ወረዳ ፍርድ ቤት
cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Computer and Accessories cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx House Furniture cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Office Furniture cttx, cttx Office Machines and Accessories cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Shoes and Other Leather Products cttx, cttx Stationery cttx, cttx Textile, Electromechanical and Electronics cttx, Garment and Leather cttx, Garments and Uniforms cttx