Your cart is currently empty!
ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ገልባጭ መኪና፣ የተለያዩ የመስኖ ዕቃዎች፣ የተለያዩ የሕንፃ መሣሪያዎች፣ የተለያዩ የኤሌክትሪክ ዕቃዎችን እና የገልባጭ መኪና ኪራይ በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 01, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር: ጣበስፋ /አግ/ብግጨ/02/2018
ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ
- በሎት–1 ገልባጭ መኪና ግዥ
- በሎት 2 የተለያዩ የመስኖ ዕቃዎች
- በሎት–3 የተሊያዩ የሕንፃ መሣሪያዎች
- በሎት 4 የተለያዩ የኤሌክትሪክ ዕቃዎችን እና
- በሎት-5 የገልባጭ መኪያ ኪራይ በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊ የ2017 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የታክስ ክሊራንስና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ/ የምስከር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፤ ለተጨማሪ እሴት ታከስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ በተጨማሪም ተጫራቾች የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ አግባብነት ያለው አካል ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
2. ጨረታው መስከረም 06 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል፡፡ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በተራ ቁጥር 4 በተገለፀው አድራሻ መስከረም 06 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂ. ቁጥር 1000057735167 በመከፈልና የባንክ አድቫይስ በማቅረብ በተራ ቁ. 4 ከተመለከተው ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
4. የጨረታው ማስረከቢያና መከፈቻ አድራሻ ቀጥሎ የተመለከተው ነው፡፡
አዲስ አበባ ቶታል 3 ቁጥር ማዞሪያ ተዘንአ ሆስፒታል አካባቢ
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንጻ።
ብሎክ A ቢሮ ቁጥር B008
ስልክ ቁጥር 011 558 6725
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ የጠቅላላ ዋጋውን 2% ብር በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ ሲፒኦ(CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ባልተመሠረተ የባንከ ዋስትና (ጋራንቲ) ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
6. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ነው፡፡
7. የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት ነው፡፡
ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 558 6725 ደውሎ መጠየቅ ይችላል።
የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ