Your cart is currently empty!
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በካፋ ዞን የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት እና የቦንጋ ከተማ ግብርና ጽ/ቤት የቦንጋ ከተማ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የባህል ልብስ እንዲሁም የዶሮ መኖ በዚህ ንግድ ዘርፍ ከተሰማሩ ድርጅቶች ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 01, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በካፋ ዞን የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት እና የቦንጋ ከተማ ግብርና ጽ/ቤት የቦንጋ ከተማ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በሎት 1 የባህል ልብስ እንዲሁም በሎት 02 የዶሮ መኖ በዚህ ንግድ ዘርፍ ከተሰማሩ ድርጅቶች ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ለመሳተፍ የሚትፈልጉ አመልካቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባችሁ፤
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣
- የግብር ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- ከገቢዎች ባለስልጣን የቲን ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
- በሎት 01 ተጫራቾች በ2017 ዓ/ም የሰሩበት የመልካም ስራ አፈፃፀም ማቅረብ የሚችሉ፣
- የጨረታው ሰነድ የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ በአካውንት ቁጥር 1000705880682 በማስያዝ ከካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 መግዛት ይቻላል።
- በዚህ የጨረታ ማስታወቅያ ላይ ያልተገለፁ መረጃዎች በጨረታ ዶክመንት ላይ ያሉት ገዥ ይሆናሉ።
- የጨረታ ሰነዱ በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከአንድ ኦሪጅናል ቴክኒካልና ፋይናንሻል እንዲሁም ከአንድ ኮፒ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ተዘጋጅቶ የሚቀረብ ሲሆን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
- የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታ መክፈቻ ሰዓት ያለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት አያስተጓጉለውም።
- የጨረታው መከፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ለሁለቱም ሎቶች 30,000 /ሠላሳ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በፖስታ ታሽጎ የሚገባውም ሆነ የሚከፈተው በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ፋይ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 ይሆናል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 047-331 0807/805 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፣
በካፋ ዞን የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ፋይ/ኢኮ/ስ/ጽ/ቤት