በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ ዞን ቀርጫ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ፈርኒቸሮች፣ የጽህፈት መሳርያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የጽዳት መሳሪያዎች፣ ሞተር ሳይክል፣ የሞተር ሳይክል ጎማ እንዲሁም መለዋወጫዎች፣ የኤሌክትሪክ ጀኔሬተር እና የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 02, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ ዞን ቀርጫ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ለ2018 በጀት አመት የሚያገለግሉ የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች የተለያዩ ቋሚ የቢሮ እና አላቂ ዕቃዎች

  1. ፈርኒቸሮች
  2. የጽህፈት መሳርያዎች
  3. ኤሌክትሮኒክስ
  4. የጽዳት መሳሪያዎች
  5. ሞተር ሳይክል፡ የሞተር ሳይክል ጎማ እንዲሁም መለዋወጫዎች
  6. የኤሌክትሪክ ጀኔሬተር
  7. የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ ከላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በዘርፍ የስራ ፍቃድ ያላችው ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርት ካሟሉ መወዳደር ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ የሥራ ፊቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ።
  2. ተጫራቾች ለተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT)ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 (አሥራ አምስት) የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 750 (ሰባት መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል በቀርጫ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10000 (አስር ሺ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከኦርጅናል ጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት።
  5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በግልጽ በመጻፍ ኮፒና ኦርጅናሉን በመለየት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ወስጥ ማስገባት አለበት።
  6. ጨረታው በ15/01/2018 ዓ.ም 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡00 ሰዓት ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሉቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት በቀርጫ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ይከፈታል።
  7. አሸናፊው አካል እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለተሸናፊ ወዲያውኑ ይመለሳል።
  8. አሸናፊ በጨረታ መመሪያ መሰረት አሸናፊነቱ በጽሁፍ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ10 ቀን ውስጥ ለጨረታ ውል መስከበሪያ የሚውል ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተመሰከረ ቼክ (CPO) ወይም ጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል መፈራረም አለበት። ይህ ባይፈጸም ቀደም ሲል ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
  9. ያሸነፉትን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት እስከ መ/ቤቱ ግምጃ ቤት ማምጣትና ፈርኒቸር ዕቃዎችን በራሱ ወጪ ማገጣጠም የሚችል።
  10. መስርያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጀ፡-ሞባይል ቁጥር 0916172339 ወይም 0911136817

በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ ዞን ቀርጫ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት