Your cart is currently empty!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎች እና አገልግሎቶችን ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 02, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በዝርዝር የቀረቡትን የተለያዩ ዕቃዎች እና አገልግሎቶችን ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ከታች በዝርዝር የተገለጹ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡–
1. ተጫራቾች የዘመኑን በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2. ተጫራቾች የቫት ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች በአቅራቢነት መመዝገባቸውን የሚገልጽ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
5.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከታች በተገለጸው መጠን መሰረት “በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ’’ ስም በተሰራ ሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ተ.ቁ |
የዕቃ ግዥው አይነት |
የግዥው ምድብ |
የግዥው ሎት ምድብ |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ብር |
የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
1 |
የስፖርት ትጥቅ ዕቃዎች ግዥ |
ዕቃ |
ሎት 1 |
150,000.00 ብር |
በ11ኛው ቀን 4፡30 |
2 |
የስፖርት ቁሳቁስ ዕቃዎች ግዥ |
ዕቃ |
ሎት 2 |
150,000.00 ብር |
በ11ኛው ቀን 4፡30 |
3 |
የስፖርት ሽልማት ዕቃዎች ግዥ |
ዕቃ |
ሎት 3 |
100,000.00 ብር |
በ11ኛው ቀን 4፡30 |
4 |
የስፖርት መስሪያ ማሽን ዕቃዎች ግዥ |
ዕቃ |
ሎት 4 |
200.000.00 ብር |
በ11ኛው ቀን 4፡30 |
5 |
የታሸገ ውሃ ግዥ |
ዕቃ |
ሎት 5 |
60,000.00 ብር |
በ11ኛው ቀን 4፡30 |
6 |
የፈርኒቸር ዕቃዎች ግዥ |
ዕቃ |
ሎት 6 |
120,000.00 ብር |
በ11ኛው ቀን 4፡30 |
7 |
የሙዚቃ መሳሪያ ዕቃዎች ግዥ |
ዕቃ |
ሎት 7 |
120,000.00 ብር |
በ11ኛው ቀን 4፡30 |
8 |
የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ |
ዕቃ |
ሎት 8 |
150,000.00 ብር |
በ11ኛው ቀን 4፡30 |
9 |
የባህል አልባሳት ዕቃዎች ግዥ |
ዕቃ |
ሎት 9 |
75,000.00 ብር |
በ11ኛው ቀን 4፡30 |
10 |
የደንብ ልብስ |
ዕቃ |
ሎት 10 |
50,000.00 ብር |
በ11ኛው ቀን 4፡30 |
11 |
የተሸከርካሪ ባትሪ ግዥ |
ዕቃ |
ሎት 11 |
25,000.00 ብር |
በ11ኛው ቀን 4፡30 |
12 |
የተሽከርካሪ ልብስ እና ተያያዥ አገልግሎቶች |
ዕቃ |
ሎት 12 |
40,000.00 ብር |
በ11ኛው ቀን 4፡30 |
13 |
የህትመት አገልግሎት ግዥ |
አገልግሎት |
ሎት 1 |
75,000.00 ብር |
በ11ኛው ቀን 9፡30 |
14 |
የጋራዥ አገልግሎት ግዥ |
አገልግሎት |
ሎት 2 |
60,000.00 ብር |
በ11ኛው ቀን 9፡30 |
15 |
የድንኳን፤ ዲኮር እና ተያያዥ አገልግሎቶች |
አገልግሎት |
ሎት 3 |
75,000.00 ብር |
በ11ኛው ቀን 9፡30 |
16 |
የኤቨንት/ኩነት/ አገልግሎት |
አገልግሎት |
ሎት 4 |
75,000.00 ብር |
በ11ኛው ቀን 9፡30 |
17 |
የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት |
አገልግሎት |
ሎት 5 |
30,000.00 ብር |
በ11ኛው ቀን 9፡30 |
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ለእያንዳንዳቸው በመክፈል ከቢሯችን ከግዥ እና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በአዲሱ ህንጻ 4ኛ ፎቅ በመቅረብ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን አሟልቶ ፋይናንሻል ዶክመንት ኦርጂናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ እንዲሁም ቴክኒካል ዶክመንት ኦርጂናል እና ኮፒ በተለያየ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
8. ጨረታው አየር ላይ በዋለ ለዕቃ ግዥ በ11ኛው የስራ ቀን በ4፡00 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚያው እለት ከጠዋቱ 4፡30 እንዲሁም ለአገልግሎት ግዥ በ4፡00 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚያው እለት ከሰዓት 9፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
9. የጨረታ አሸናፊው እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለአሸናፊዎች ከ7 ቀን በኋላ ይመለሳል፡፡
10. የጨረታ አሸናፊው በተጫራቾች መመሪያ በተጠቀሰው መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በጽሁፍ በተገለጸ ከ7 /ሰባት/ ቀናት በኋላ አስፈላጊውን የውል ማስከበሪያ ገንዘብ በመያዝ ወዲያውኑ ወደ ስራ ክፍሉ መጥቶ ውል መፈረም አለበት ይህ ባይፈጸም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡
11. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ማስታወሻ
- አንድ ሰነድ የሚያገለግለው ለአንድ የሎት አይነት ብቻ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡– በስልክ ቁጥር 011 812 0778
አድራሻ፡– ፍላሚንጎ ምርጫ ቦርድ አጠገብ ባ/ኪ/ቱ ህንፃ ላይ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ