በዶዶላ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው የዶዶላ 2ኛ ደረጃ ልዩ አዳሪ ት/ቤት በ2018 ዓ.ም የተለያዩ ዕቃዎች ለልዩ ልዩ ት/ቤት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 02, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2017

በዶዶላ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው የዶዶላ 2ኛ ደረጃ ልዩ አዳሪ ት/ቤት በ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለፁትን ዕቃዎች ለልዩ ልዩ ት/ቤት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  1. የፅህፈት መሳሪያ ዕቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ አላቂ ዕቃና የትምህርት ዕቃዎች፣
  2. የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣
  3. የተማሪዎች ዩኒፎርም፣ የሠራተኛ ደንብ ልብስና የስፌት አገልግሎት
  4. የተለያዩ የህትመት አገልግሎት።
  5. የተማሪዎች የምግብ አገልግሎት ዕቃዎች፣ የተማሪዎች የምግብ አቅርቦት፣ ለተማሪዎች የምግብ አቅርቦት የሚሆኑ ሰብሎች/እህሎች ፍራፍሬዎችና ለወጣወጥ የሚሆን ጥራጥሬዎች
  6. የመኪና እቃዎች፣ የመኪና ጎማ፣ የመኪና ጥገና
  7. ሞተር ሳይክል፣ ባለሶስት እግር ባጃጅና የሳር ማጨጃ ማሽን።

በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው።

  1. ተጫራቾች ከሚጫረቱበት ዕቃ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለውና ዕቃዎቹን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ VAT እና TIN No. እንዲሁም የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ብቻ።
  2. ተጫራቾች በጨረታተካፋይ ለመሆን የሚፈልጉት በምን ዓይነት ዕቃ እንደሆነ በሰነዶቻቸው ላይ በትክክል ለይተው መጻፍ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የዕቃ ስም /Brand Name/ እና የተመረተበትን ሀገር መግለጽ ይኖርባቸዋል።
  4. ማንኛውም ተጫራች የሚወዳደርበትን የዕቃ ዓይነት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርበታል። በነጠላ ዋና ጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ቢኖር የነጠላ ዋጋ ይወሰዳል።
  5. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ በ15 የስራ ቀናት ውስጥ ቅዳሜ፣ እሁድና የበዓላት ቀን ሳይጨምር በተ.ቁ 1-4 ለተጠቀሱት የማይመለስ 100.00 ብር በዶዶላ 2ኛ ደረጃ ልዩ አዳሪ ት/ቤት በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸው ላይ መ/ቤታችን በሰጣቸው የጨረታ ሰነድ ላይ የአንዱ ዋጋ የሚለው ቦታ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ ያካተተ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላትና የድርጅታቸውን ማህተም በየገፁ፣ ፊርማና ሙሉ አድራሻቸውን በመግለፅ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ኮፒ በሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 3 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  7. ለጨረታ ከቀረቡ ዕቃዎች ዝርዝር ውስጥ ጽ/ቤቱ እስከ 20% ለመጨመር ወይም ለመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ተመላሽ የሚሆን በተ.ቁ 1፣ 2ና 3 ብር 10,000.00 እንዲሁም በተ.ቁ 4 ብር 5000.00 በባንክ የተመሰከረለት (CPO) ወይም ጥሬ ብር በዶዶላ 2ኛ ደረጃ ልዩ አዳሪ ት/ቤት ማስያዝ አለበት።
  9. የሚቀርቡት ዕቃዎች ጥራት ያላቸውና በተሰጠው ስፔስፊኬሽን መሰረት ተሟልተው መቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ውል በሚፈርሙበት ጊዜ አጠቃላይ ካሸነፉት ዕቃ ላይ የውል ማስከበሪያ ተመላሽ የሚሆን 10% በጽ/ቤቱ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
  10. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት እስከ ዶዶላ 2ኛ ደረጃ ልዩ አዳሪ ት/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
  11. በተ.ቁ 1, 2, 3, 4 ና 5 ውስጥ በመ/ቤታችን የተገለፁት ዕቃዎች ጨረታውን ከመከፈቱ በፊት የሚመለስ ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
  12. ጨረታው በ27/12/2017 ዓ.ም በአየር ላይ ውሎ በ14/01/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 3 ውስጥ ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያግድም። ዕለቱ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
  13. ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  14. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 13 40 60 64/ 09 16 42 38 65 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

በዶዶላ ከተማ አስተዳደር የዶዶላ 2ኛ ደረጃ ልዩ አዳሪ ት/ቤት