የአማራ ብሔ/ክ/መ/የሰ/ሸዋ/ዞን የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ግ/ን/አስ/ቡድን ለተለያዩ ሴ/መስሪያ ቤቶች ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ጥገናዎች እና ቋሚና አላቂ እቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 02, 2025)

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2017

የአማራ ብሔ///የሰ/ሸዋ/ዞን የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ገንዘብ /ቤት //አስ/ቡድን ለተለያዩ /መስሪያ ቤቶች 2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ጥገናዎች እና ቋሚና አላቂ እቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል።

  • የመኪና ጎማ ሎት 1 የጨረታ ማስከበሪያ 30,000ብር
  • የስፖርት አልባሳትና ጫማዎች ሎት 2 የጨረታ ማስከበሪያ 4000ብር
  • የስፖርት እቃዎች መገልገያዎች ሎት 3 የጨረታ ማስከበሪያ 4000 ብር
  • የኤሌክትሮኒክ ወይም የማሽን ጥገና ከነመለዋወጫው እቃ ጭምር ሎት 4 የጨረታ ማስከበሪያ 3000ብር
  • የመኪና መለዋወጫ ሎት 5 የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 ብር
  • የመኪና ጥገና ሎት 6 የጨረታ ማስከበሪያ 6000 ብር

ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ 27/12/2017 . እስከ 07/01/2017 . 15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ 16 ኛው ቀን በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 400 ሰዓት ተዘግቶ ወዲያውኑ 430 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤

1. በጨረታው የሚሣተፍ በዘመኑ የታደሠ የንግድ ስራ ፍቃድ፣ የግብር ከፉይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ የቫት ተመዝጋቢ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ መረጃውን አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. በሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ላይ የጨረታ መዝጊያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ራሣቸውን ከጨረታው ማግለል አይችሉም፡፡

3. ተጫራቾች የሞሉበትን የጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዙበትንም ደረሠኝ ከሆነ ፎቶ ኮፒ አድርገው ማቅረብ አለባቸው CPO ከሆነ ዋናውን ማቅረብ አለባቸው።

4. የንግድ ፍቃድና የመሣሠሉት መረጃዎች ከኦርጅናል ዶክሜንት ጋር ተያይዘው መቅረብ አለባቸው፤ በፖስታው ላይና እንዲሁም በጨረታ ዋጋ መሙሊያ የጨረታ ሠነድ ላይ የተጫራቾች ስምና ፊርማና ማህተም ሊኖረው ይገባል።

5. በሌላ ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም እንዲሁም ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡

6. ተጫራቾች አሽናፊነታቸው በተገለፀላቸው 5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በጽ/ቤታችን በመገኘት የውል ማስከበሪያ 10% በማሲያዝ ውል መፈፀም አለባቸው በተሠጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርበው ውል ካልፈፀሙ በግዥ መመሪያው መሠረት የጨረታ ማስከበሪያውን ውርስ በማድረግ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።

7. ተጫራቾች በጨረታ አፈፃፀም ሂደት ላይ ቅሬታ ካላቸው በግዥ አዋጅ መሠረት አሸናፊነቱ በተገለፀው በተከታታይ 5 የስራ ቀን ውስጥ ቅሬታቸውን ማቅረብ ይችላሉ።

8. ለአሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዙትን ብር ከአሽናፊ ተጫራች ጋር ውል እንደተፈፀመ ተመላሽ ይደረጋል።

9. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን ሁሉንም ተጫራቹ መሙላት አለበት፤ ሁሉንም ካልሞሉ ከውድድር ውጪ ይደረጋል።

10. ጨረታው በሚከፈትበት ወቅት የህዝብ በዓላት፣ ቅዳሜና እሁድ ከዋለ በቀጣዩ የስራ ቀናት በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

11. የጨረታ ሰነዱን በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ገንዘብ /ቤት ድረስ በመምጣት ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በማይመለስ መግዛት የሚቻል ሲሆን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛትና መውሰድ ይችላሉ።

12. ሂሳብ የሚከፈለው አሸናፊው ተጫራች በውሉ መሰረት እቃዎቹን ሲያጠናቅቅ ክፍያውን ይወስዳል።

13. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

14. አሸናፊ የሚለውየው በጥቅል ወይም በተናጠል /ቤቱ በሚያዋጣው ነው።

15. የስፖርት ትጥቅ እና ኳስ ሳምፕል ለሚያስፈልጋጣ ሳንፕሉን በማየት ዋጋ በመሙላት ማቅረብ አለባቸው።

16. 200,000 ሺህ ብር በላይ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለበት።

17. ተጨማሪ ማብራሪያ ሲፈልጉ በስልክ ቁጥር 011 685 1461 /0106 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።

18. ለጥቃቅን የተደራጁ ኢንተርፕራይዝ ልዩ አስተያየት የሚደረግ ሲሆን ካደራጃቸው /ቤት ስንት ዓመት እንደሞላቸው አያይዘው ከሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው::

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት /ቢሮ በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ገንዘብ /ቤት