Your cart is currently empty!
በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ ቋሚና አላቂ እቃዎችን በ2018 ዓ.ም በጀት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 02, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ ቋሚና አላቂ እቃዎችን በ2018 ዓ.ም በጀት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች
1. በየመንግስት እቃ አቅራቢነት ተመዝግበው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. በዘርፍ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው ፡፡
3. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
4. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
5. በሚወዳደሩበት የሎት አይነት ላቀረበው ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ጨረታ ላቀረበው ጠቅላላ ዋጋ (2%) የጨረታ ማስከበሪያ በተቋማችን (በጽ/ቤታችን) ስም አሰርቶ ማቅረብ የሚችል
6. ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት በወረዳ 01 ፋ/ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 21 በመገኘት የማይመለስ 200/ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ጨረት ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ ዋጋ በመሙላትና በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
8. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ ከ3፡30 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
10. ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ(CPO) በየካ/ክ/ከተማ ወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት በሚል ስም አሰርቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ ፡– በስልክ ቁጥር 011 154 8607/ 011 154 0036 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
አድራሻ፡– የካ/ክ/ከ ወረዳ 01 ፋ/ጽ/ቤት ፈረንሳይ ለጋሲዎን ወደ 41 እየሱስ በሚወስደው መንገድ
በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት