Your cart is currently empty!
የሰበታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ሥራ አገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ አላቂ እቃዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ የመኪና ጎማዎችን፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 02, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የሰበታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ሥራ አገልግሎት የሚውሉ
- ሎት1 የጽህፈት መሳሪያዎች፣የጽዳት እቃዎች፣አላቂ እቃዎች፣ የደንብ ልብሶች
- ሎት 2. የመኪና ጎማዎችን፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይገልፃል።
1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የታደሰ እንዲሁም የሚፈለግባቸውን የዘመኑን ግብር አጠናቀው ስለመክፈላቸው በቂ ማስረጃ (ክሊራንስ) ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ከገቢዎች ባለስልጣን በተወከለው ሠራተኛ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ወደ ሲንቄ ባንክ ሂሳቡ ቁጥር በSebeta Sub city Finance Office “A” 1064814111214 ገቢ በማድረግ ክፍለ ከተማ ገቢዎች በመሄድ ወደ ደረሰኝ በማስቀየር ዘወትር በስራ ሰዓት በሰበታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ፋይናንስ ግዥ እና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት መግዛት ይችላል፡፡
3. ተጫራቾች የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ለተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት በተዘጋጀው ሰንድ ብር 10,00.00 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት CPO ብቻ በሰበታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ስም አዘጋጅተው ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
5. ተጫራቾች ሰነዱን ከገዙ በኋላ የሚሸጡበትን ዋጋ በመጥቀስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናል እና ኮፒ ሰነድ ለብቻ በማሸግ በተባለው ቀን ውስጥ ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል እንዲሁም ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ቫትን 15% ያካተተ መሆን አለበት፡፡
6. ለጨረታ የሚያቀርቡት በእያንዳንዱ ሰነዱ ገጽ ላይ የድርጅቱን ስምና አድራሻ የሚገልጽ ሕጋዊ ማህተምና ፊርማ መስፈር አለበት።
7. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው ቦታ ድረስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
8. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች ገቢ የሚሆነው አስፈላጊው ጥራት ማሟላቱ በባለሙ እና ጥራት አጣሪ ኮሚቴ ሲረጋገጥ ብቻ ይሆናል፡፡
9. ተጫራቾች የሚያቀርቡት እቃ ከስቶክ ወይም ከራሳቸው ስቶር መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
10. ተጫራቾች የሚያቀርቡት እቃ ጥራት የጠበቀ መሆን አለበት፡፡
11. ተጫራቾች የሚያቀርቡት እቃ የሎት አንድ(1)2 ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙናውን ማቅረብ አለባቸው፡፡
12. የጨረታውን ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናት የሚሸጥ ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በተጠቀሰው ቀን 4፡30 የሚከፈት ይሆናል፡፡
13: ከላይ የተገለጸው የመክፈቻ ቀን በዓል ወይንም የሰንበት ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በቀጣዩ የስራ ቀን ይሆናል፡፡
14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁር 011 366 2199(09 13 65 85 63)
በሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰበታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት