በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም በጀት የተለያዩ ዕቃዎች መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 02, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የአንደኛ ዙር ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር 01/2018

በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 2018 . በጀት ላይ የሚከተሉትን ዕቃዎች መግዛት ይፈልጋል።

1. ሎት – 01 የኮንስትራክሽን የሥልጠና ዕቃዎች ግዢ

2. ሎት – 02 የሰርቬይንግ የሥልጠና ዕቃዎች ግዢ

3. ሎት – 03 የአዉቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ የሥልጠና ዕቃዎች ግዢ

4. ሎት – 04 የማኑፋክቸሪንግ ሥልጠና ዕቃዎች ግዢ

5. ሎት – 05 የኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ የሥልጠና ዕቃዎች ግዥ

6. ሎት– 06 የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የሥልጠና ዕቃዎች ግዢ

7. ሎት – 07 የጽሕፈት መሣሪያዎች (STAIONERY MATERIALS)

8. ሎት – 08 የጽዳት እቃዎች ግዢ

9. ሎት – 09 የሴፍቲ ማቴሪያል የሥልጠና እቃዎች ግዥ

በዚሁ መሠረት በጨረታው ላይ መወዳደር ለሚትፈልጉ ተጫራቾች፡

1. በዘርፉ ህጋዊ የሆነና የታደሰ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

2. የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና በተወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ ላይ የአቅራቢነት ሰርትፍኬት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

3. ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡመሆኑንየሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢ ባለስልጣን የተሰጠና በጨረታ ላይ መሳተፍ የሚያስችል የእቃ አቅራቢነት ማስረጃ(ደብዳቤ) ማቅረብ አለባቸው።

4. ተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No) የሚገልፁ የምስክር ወረቀት ኮፒውን ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የሚጫረቱበት የእቃዎች ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ በሚታይ መልኩ ያለስርዝ ድልዝ በመሙላት የሞሉት ዋጋ በኢትዮጵያ ብር ሆኖ ከቫት በፊት ያለው ዋጋ መሆን አለበት።

6. ተጫራቾች በገዙት ጨረታ ሰነድ በሁሉም ገፅ ላይ የድርጅቱ ባለቤት ፊርማ ሙሉ አድራሻውንና ህጋዊ ማህተም ያረፈበት ኦሪጅናሉን እና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND) ለእያንዳንዱ ምድብ(ሎት) ከባንክ በተረጋገጠ CPO 10,000.00(አስር ሺህ) ብር ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማስገበት አለባቸው።

8. ተጫራቾች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥራቸውን የሚገልፅ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን ከኮሌጁ የግዥ እና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

10. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 345 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ተዘግቶ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ላይ ይከፈታል። በጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት ተጫራቾችም ሆኑ ህጋዊ ወኪሎቻው ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል።

11. የጨረታ መክፈቻው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ላይ ተዘግቶ የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን።

12. ተጫራቾች አንድ ተጫራች የሰጠውን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው።

13. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡-0251-13 09 52/53/54/55

ፖስታ ሳጥን ቁጥር 2601 ፋክስ ቁጥር 0251-12 45 53 ማግኘት ይችላሉ።

ተጨማሪ ማሳሰቢያ፡ ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ ባለው ዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ የሚሞሉት ዋጋ ከቫት በፊት መሆኑን እንዳይረሱት በድጋሚ ማሳሰብ እንፈልጋለን።

በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ