የካ ጣፎ የመጀ/ደ/ት/ቤት የቴክኖሎጂ እቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የት/ት እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የሰራተኛ የደንብ ልብስ፣ የህትመት፣ ፈርኒቸር፣ የኮምፒውተር ጥገና እንዲሁም ልዩ ልዩ ግዥን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 02, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ

የጨረታ ማታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡-001/2018

የካ ጣፎ የመጀ/ደ//ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

እነርሱም፡የቴክኖሎጂ እቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የት/ እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የሰራተኛ የደንብ ልብስ ግዥ፣ የህትመት ግዢ፣ ፈርኒቸር ግዥ የኮምፒውተር ጥገና እንዲሁም ልዩ ልዩ ግዥን ይመለከታል።

1. ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የሃገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ እንዲሁም በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ለመሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ብቻ በየካ ጣፎ የመጀ ቤት ፋይናንስ ግዢ ንብረት አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ወረቀትና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN No/ ማቅረብና VAT (ቫት) ከፋይ መሆን አለባቸው፡፡

4. ተጫራቾች በጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተመላሽ የሚሆን ብር በባንከ በተመሰከረለት የክፍያ

ትዕዛዝ ሲፒኦ ሎት 1 – 3,000 ብር፣ ሎት 2 – 5,000 ብር፣ ሎት 3 – 1,000 ብር፣ ሎት 4 – 3,500 ብር፣ ሎት 5 – 1,500 ብር፣ ሎት 6 – 4,000 ብር፣ ሎት 7 – 8,000 ብር፣ ሎት 8 – 10,000 ብር ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን አንስቶ 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ ቀኑ 1030 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ እና ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራቾች ከዋናው ሰነድ በተጨማሪ ፋይናንሻያል እና ቴክኒካል ሰነዳቸውን ኮፒውን እና ኦሪጂናሉን ማስገባት አለባቸው።

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማሸግ እና በላዩ ላይ የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይኖርባቸዋል።

8. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ እቃ ነጠላ ዋጋ በቀረበው ሰነድ ላይ 15% ቫትን ጨምረው መሙላት ይኖርባቸዋል።

9. የጨረታው አሸናፊዎች ማሸነፋቸው በፅሁፍ የሚገለጽላቸው ሲሆን ለጨረታ አፈፃፀም ውል ማስከበሪያ ላሸነፉበት እቃ ዋጋ 10% በታወቀ ባንክና በተመሰከረለት ሲፒኦ በማስያዝና ውል የመዋዋል ግዴታ አለባቸው፡፡

10. የጨረታ ማስከበሪያና የውል ማስከበሪያ ደብዳቤ የምታጽፉ ጥቃቅንና አነስተኛ አቅራቢዎች የተሰማራችሁበትን የንግድ ስራ መስክ /ዘርፍ/ የሚገልጽ መሆን አለበት። እንዲሁም የፈጠረና ክህሎት ሚኒስቴር ያደራጃቸው መሆኑና በሚያመርቱት ምርት ብቻ እንዲወዳደሩ እናሳውቃለን፡፡

11. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ ስትመልሱ ሙሉ አድራሻችሁን በተሰጠው የመጫረቻ ሰነድ ላይ በትክክል መሙላት ይኖርባችኋል።

12. /ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊልም የመሰረዝ መብት አለው።

13. ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ 60 ቀናት ብቻ ነው፡፡

14. በጨረታ ሰነድ የቀረበው የእቃ ብዛት /ቤቱ 20% መጨመርና መቀነስ ይችላል።

15. ተጫራቾች ተወዳድረው ካሸነፉ በኋላ ከናሙናው ምንም አይነት ለውጥ ሳያደርጉ በራሳቸው ወጪ ጭነው ማቅረብና ደረጃውን ያልጠበቀ እቃ ከሆነ መልሰው ትክክለኛውን በቀረበው ናሙና መሰረት የማምጣት ግዴታ አለባቸው፡፡

16. ተጫራቾች ጨረታውን ሲያሥገቡ ለእያንዳንዱ እቃዎች ናሙና ማስገባት ይኖርባቸዋል።

17. በ11ኛው ቀን 400 ሰዓት ታሽጎ 430 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይከፈታል።

18. ለመምህራን ጋወን ደንብ ልብስ (50cm*50cm) ቁራጭ ጨርቅ ማስገባት እና 27.50 ያርድ የሆነ፤

19. የእንስታሌሽን/ ፕላንት ተከላ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሳይንስ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ ቢያንስ እስካሁን 3 እና ከዚያ በላይ የምስጋና ሰርተፊኬት የሚያቀርቡ፤

ልዩ ቦታው፡ከአያት ወደ ጣፎ በሚወስደው መንገድ ከገ/ቤተከርስቲያን አለፍ ብሎ ይገኛል።

የካ ጣፎ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ /ቤት