የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጀንሲ ለ2018 በጀት አመት የሚገለገልባቸውን የተለያዩ አይነት የአገልግሎቶች እና የእቃ ግዥዎችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 02, 2025)

የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጨረታ መለያ ቁጥር፡///አስ/ምገባ ኤጀንሲ/.././01/2018 እና ///አስ/ምገባ ኤጀንሲ/../አገ./02/2018 ምገባ ኤጀንሲ 2018 በጀት አመት የሚገለገልባቸውን የተለያዩ አይነት የአገልግሎቶች እና የእቃ ግዥዎችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ ፈቃደኛ የሆናችሁ ተጫራቾች እንድትሳተፉ እየጋበዝን እቃዎቹ እና አገልግሎቶቹ እንደሚከተሉት ተዘርዝረዋል፡፡

ምድብ ቁጥር

የሚገዛው እቃ/አገልግሎት/ አይነት

የጨረታ ማስከበሪያ ብር

ሎት 1

የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ

25,000 ብር

ሎት 2

የፅዳት እቃዎች ግዥ

7,000 ብር

ሎት 3

የፅህፈት መሳሪያዎች ግዥ

12,000 ብር

ሎት 4

የኘሪንተር እና የፎቶ ኮፒ ቀለም ግዥ

8,000 ብር

ሎት 5

የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አበባ ግዥ

5,000 ብር

ሎት 6

የደንብ ልብስ እና ስፌት አገልግሎት ግዥ

2,000 ብር

ሎት 7

መጋረጃ እና የወለል ምንጣፍ ግዥ

2,000 ብር

ሎት 8

የመኪና እቃዎች እና አልባሳት ግዥ

10,000 ብር

ሎት 9

የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ

20,000 ብር

ሎት 10

የህትመት ስራ አገልግሎት ግዥ

18,000 ብር

ሎት 11

የመስተንግዶ አገልግሎት ግዥ

15,000 ብር

ሎት 12

የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና አገልግሎት ግዥ

10,000 ብር

ሎት 13

የአጥር የኤሌክትሪክ ጥገና እና የፓርቲሽን ስራ አገልግሎት ግዥ

20,000 ብር

ሎት 14

የፈርኒቸር እቃዎች እና ሌሎች የጥገና አገልግሎት ግዥ

15,000 ብር

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፡፡

3. ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300/ ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የምትወስዱ መሆኑን እየገለፅን ይህ ጨረታ በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆናል፡፡

5. ጨረታው ሰነድ መመለሻ የመጨረሻ ቀን 07/01/2018 . 830 ሰዓት ነው

6. ጨረታው በቀን 07/01/2018 . 330 ሰዓት ተዘግቶ በቀን 07/01/2018 . 400 ሰዓት ይከፈታል

7. ተጫራቾች ሌሎች መረጃዎችን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

8. ኤጄንሲው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

9. የጨረታ ሰነዱ ፒያሳ ኤሊያና ሆቴል ፊት ለፊት(ዶን የጥርስ ህክምና) ያለበት ህንጻ ላይ 8 ፎቅ ግዥና ንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይገኛል

አድራሻ፡ ፒያሳ ኤሊያና ህንጻ ፊት ለፊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቤተክህነት (ዶን የጥርስ ህክምና ያለበት) ህንጻ ላይ 8 ፎቅ የግዥና ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር +251-11-812 8321

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጀንሲ