Your cart is currently empty!
በደ/ምዕ/ኢት/ህ/ክ/መ/በካፋ ዞን ቢጣ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ቁሳቁሶችንና ጥገናዎችን ማለትም ጽ/መሣሪያ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የግንባታ ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የእንስሳት መድሐኒት፣ ፈርኒቸር፣ የፕሪንተር ቀለሞችን እና የመኪና ጥገናዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 08, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ምዕ/ኢት/ህ/ክ/መ/በካፋ ዞን ቢጣ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ቁሳቁሶችንና ጥገናዎችን ማለትም 1ኛ. ጽ/መሣሪያ በሎት 2ኛ, ኤሌክትሮኒክስ 3ኛ የግንባታ ዕቃዎች 4ኛ.የደንብ ልብስ 5ኛ. የእንስሳት መድሐኒት 6ኛ. ፈርኒቸር 7ኛ የፕሪንተር ቀለሞችን 8ኛ የመኪና ጥገናዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ፡– በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች፡–
1. የዘመኑን ግብር የከፈሉና በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
2. የዕቃና አገልግሎት አቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
3. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ16ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በእለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 በግልጽ ይከፈታል፡፡ወኪሎቻችሁ ቢገኙም ባይገኙም የጨረታው ሂደት አይስተጓጎልም፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ በማይመለስ ብር 300 በመግዛት የመወዳደሪያ ዋጋችሁን በተዘጋጀው ሠነድ /specification / መሰረት በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ/ ፖስታ ኦርጅናሉንና ኮፒውን በማመሳከር ለየብቻ በማሸግ በቢጣ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
5. የጨረታው አሸናፊዎች ዕቃውን የማስረከቢያ ቦታ በመ/ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በካሽ ለእያንዳንዱ ከላይ ከ1 እስከ 8 ላሉት ዝርዝር መወዳደሪያ ሠነድ 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪ የጨረታ ማስከበሪያው ከኦርጅናል ቴክኒካል ዶክመንት ጋር መታሸግ አለበት ፡፡
7. መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 047 773 0018/17/19 ደውለው ይጠይቁን።
ማሳሰቢያ ፡– ተጫራቾች የጨረታውን 2 % ቅድመ ታክስ ታሳቢ ዊዝሆልድ የሚሆን መሆኑን እንገልጻለን
በካፋ ዞን የቢጣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት