Your cart is currently empty!
የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አ.ማ ተበዳሪዎች የተበደሩትን ገንዘብ በብድር ውላቸው መሠረት መክፈል ስላልቻሉ ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በመሸጥ ገንዘቡን ወደ ተበዳሪዎች የብድር ዕዳ ገቢ ለማድረግ ይፈልጋል
Reporter(Sep 07, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ለመጀመሪያ እና ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አ.ማ ተበዳሪዎች የተበደሩትን ገንዘብ በብድር ውላቸው መሠረት መክፈል ስላልቻሉ ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና በማሻሻያ አዋጁ ቁጥር 216/2000 በሕግ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለብድሩ መክፈል ዋስትና/መያዣ እንዲሆኑ ሥልጣን ባለው የመንግስት አካል የተመዘገቡትን እና ያሳገደዉን ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በመሸጥ ገንዘቡን ወደ ተበዳሪዎች የብድር ዕዳ ገቢ ለማድረግ ይፈልጋል::
ስለዚህ ማንኛውም ተጫራች ሐራጁ በሚካሄድበት ቦታ እና ዕለት በመቅረብ በጨረታው ላይ እንዲወዳደር ተጋብዟል::
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
የንብረት አስያዥ ስም |
የንብረቱ ዓይነት |
አበዳሪው ቅርንጫፍ |
የንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ |
የካርታ ቁጥር |
የቦታ ስፋት |
የጨረታ መነሻ ዋጋ |
ጨረታዉ የሚካሄድበት ቦታና ሰዓት |
|
|
ከተማ |
ክ/ከተማ /ቀበሌ |
|||||||||
|
1 |
አቶ ገዛኃኝ ደሳለኝ ጂማዩ |
አቶ ገዛኃኝ ደሳለኝ ጂማዩ |
የመኖሪያ ቤት |
አባ ነብሶ |
ቢሾፍቱ |
ዱከም |
OR0090 41805010 |
140 ካ.ሜ |
5,949,288.22 |
ጨረታው መስከረም 28 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት ከ4፡00-6፡00 ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ለመጀመሪያ ጊዜ ይካሄዳል:: |
|
2 |
አቶ መስፍን ታደሰ ሙለታ |
አቶ መስፍን ታደሰ ሙለታ |
የንግድ ህንጻ/ ለሆቴል አገልግሎት የሚውል/G+4/ |
ኦዳ |
ነጆ |
02 |
660/2006 |
709.04 ካ.ሜ |
52,282,500.12
|
ጨረታው መስከረም 28 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት ከ4፡00-6፡00 በኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ነጆ ቅርንጫፍ ውስጥ ለሁለተኛ ዙር ይካሄዳል:: |
ተጫራቾች እንዲያውቋቸው፡–
1. ተጫራቾች ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4 (25%) የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ በኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አ.ማ ስም አሰርተው ሀራጁ በሚካሄድበት አድራሻ ቀርበው በመመዝገብ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ:: ጨረታውን በድርጅት ስም የሚጫረት ተጫራች በዘመኑ የታደሰ ንግድ ምዝገባ፣ ንግድ ፈቃድና የድርጅቱን ውክልና እና የታደሰ መታወቂያ ይዞ መቅረብ አለበት፤
2. ጨረታው ከላይ ቀንና ሰዓቱ በተገለፀው መሠረት ባለዕዳዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይካሄዳል፤ ባለዕዳዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ሳይገኙ ቢቀሩ ግን ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል፤
3. ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት መጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ለተ.ቁ 1 በስ.ቁ 09-12-04-15-52/09-13-03-83-83፤ ለተ.ቁ 2 በስልክ ቁጥር 0912-774669/0912-441524 በመደወል ተጨማሪ ማብራሪያ/መረጃ ማግኘት ይችላሉ፤
4. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15(አሥራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል አለበት:: በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ እንዲቀርብ ይደረጋል:: በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረጋል፤
5. የጨረታው አሸናፊ በሕጉ መሠረት ለመንግስት የሚከፈለውን ማንኛውንም የቫት(ካለ) እና ታክስ ክፍያ፣ የስም ማዛወሪያ እና ሌሎች ወጪዎችን ከፍሎ ስሙን ወደ ራሱ እንዲዛወር ያደርጋል፤
6. ባንኩ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አ.ማ