Your cart is currently empty!
በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የባሻ ወልዴ ችሎት ጤና ጣቢያ ቋሚና አላቂ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 07, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ባሻ/ወ/ች/ጤ/ጣ 01/2017 ዓ.ም
በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ባሻ ወልዴ ችሎት ጤና ጣቢያ በ2018 የበጀት አመት የሚያስፈልገውን ቋሚና አላቂ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል:: ሎት 1፡–የፅህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች፣ ሎት3፡ –ህክምና መሳሪያዎች፣ ሎት-4፡–የሠራተኞች ደንብ ልብስ እና ማሰፊያ፣ ሎት5፡ ላዉንደሪ ማሽን፣ ሎት 6 –የቢሮ ዕቃዎች እና ኮምፒውተር ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሎት 7፡–የቢሮ ፈርኒቸሮች፣ ሎት 8፡–የሰራተኞች ካፌ (መዝናኛ ክበብ)፣ ሎት.9፡–የህትመት ስራዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
ስለዚህ በጨረታው ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ መሟላት ይኖርባቸዋል።
1. ተጫራቾች በተሠማሩበት የሥራ መስክ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸውና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ።
2. ከአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምዝገባ ሰርተፍኬት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች የግብር ከፍያ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናችሁን የሚያረጋግጥ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ።
4. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ወደ መ/ቤታችን ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች በጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያገለግል የመጫረቻ ዋጋ 2% በድርጅቱ ስም ሲፒኦ በማዘጋጀት ማረጋገጫውን ከመወዳደሪያ ሠነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች በአንድ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም::
7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ በጥንቃቄ ሞልተው በመፈረምና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋና እና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አሥር/ ቀናት ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
8. መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልቶ እና የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም አድርጐ የማያቀርብ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
9. የጨረታውን አሸናፊ ማሸነፋቸውን በጽሁፍ የምንገልጽላቸው ሲሆን ለውል ማስከበሪያ ባሸነፈበት የግዥ ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝና ውል በመዋዋል የተመረጡትን እቃዎች በሙሉ በውሉ መሠረት ካላቀረቡ በግዥ ህጉ መሠረት መ/ቤቱ ተጠያቂ ያደርጋል።
10. በጨረታው ያላሸነፉት ድርጅቶች ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
11. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል እንደማይችሉ ማወቅ አለባቸው፡፡
12.ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የያዘ በየሎቱ የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ የሥራ ቀናት ውስጥ ጤና ጣቢያው ቀርበው መውሰድ ይችላሉ፡፡
13. የጨረታውን ሳጥን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ እለት ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት በአራዳ ክ/ከተማ ባሻ ወልዴ ችሎት ጤና ጣቢያ አዳራሽ በግልጽ ይከፈታል።
14.ተጫራቾች በሚጫረቱባቸው እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የካታሎግ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፣ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ናሙና ማቅረብ አይቻልም፤ ናሙና ያላቀረበ ተጫራች ከውድድር ውጪ ይሆናል።
15. ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው እቃዎች በሙሉ ኦርጅናል ሆኖ ለዚህም ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፤ መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ ፡– ስልክ ቁጥር 011 18 57 86 50
አድራሻ፡ ከቱሪስት ሆቴል ወረድ ብሎ ልቀት ኮሌጅ ፊት ለፊት
በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የባሻ ወልዴ ችሎት ጤና ጣቢያ