Your cart is currently empty!
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የወረዳ 8 ሚሊኒየም ጤና ጣቢያ የተለያዩ እቃዎችን እና አገልግሎት ስራዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 07, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር/ግ/ 001/ 2018 ዓ.ም
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የወረዳ 8 ሚሊኒየም ጤና ጣቢያ ለ2018 በጀት ዓመት ለጤና ጣቢያው አገልግሎት የሚውሉ፡
- ሎት 1 የደንብ ልብስ ግብዓቶች እና የስፌት አገልግሎት
- ሎት 2 አላቂ የፅህፈት መሣሪያዎች
- ሎት 3፡የህትመት ውጤቶች
- ሎት 4፡ ቋሚ እና አላቂ የህክምና ዕቃዎች
- ሎት 5፡ አላቂ የፅዳት ዕቃዎች
- ሎት 6፡ ልዩ ልዩ ዕቃዎችና መሣሪያዎች
- ሎት 7፡ ልዩ ልዩ የጥገና ዕቃዎች የቤት ቁሳቁስ/
- ሉት 8፡ ልዩ ልዩ የጥገና ዕቃዎች የቤት ቁሳቁስ
- ሎት 9፡ ቋሚ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች ፈርኒቸር:
- ሎት 10፡ ቋሚ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች ኤሌክትሮኒክስ/
- ሎት 11፡ ልዩ ልዩ አገልግሎቶች
- ሎት 12፡ ልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች የጥገና እና የሰርቪስ አገልግሎቶች
- ሎት 13፡ ልዩ ልዩ የጥገና እና የአገልግሎት ስራዎች
በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመሣተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች የሚከተሉትን መስፈርት አሟልቶ በጨረታው መወዳደር ይችላል፡፡
1 በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና “ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤
3. የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
4. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተመዘገቡት
5. በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘዝ ስለመሆናቸው ያቀረቡት ማስረጃ በዌብሣይት የሚረጋገጥ፤
6. እንደአስፈላጊነቱ ለአገልግሎት ስራዎች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማንኛውም ተጫራች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የወረዳ 8 ሚሊኒየም ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 407 በሚገኘው የግዢ ክፍል ቀርበው የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡ ማንኛውም ተጫራች ለሚወዳደርበት ዕቃዎቸ ናሙና በዕቃው ዓይነት ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይጠበቅበታል፡፡ ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሰረት የሚወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላት ዋና እና ኮፒ ሠነዶችን እንዲሁም ለናሙና የሚቀርቡ የዕቃውን ስም የሚገልፁ የዕቃዎች ናሙና እና የፎቶግራፎች ናሙና ለየብቻ በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ በመገኘት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ለተጫራቾች ጨረታው እንደተጠናቀቀ ተመላሽ የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን:-
ተ.ቁ |
የሎት ቁጥር |
የሎት መግለጫ |
የጨረታ ማስከበሪያ በፐርሰንት |
የጨረታ ማስከበሪያ በብር |
1 |
ሎት 1 |
የደንብ ልብስ ግብአቶች |
0.5 |
12,000.00 |
2 |
ሎት 1 |
የደንብ ልብስ የስፌት አገልግሎት |
0.5 |
500.00 |
3 |
ሎት 2 |
አላቂ የፅህፈት መሣሪያዎች |
0.5 |
7,220.00 |
4 |
ሎት 3 |
የህትመት ውጤቶች |
0.5 |
7,075.00 |
5 |
ሎት 4 |
ቋሚ እና አላቂ የህክምና ዕቃዎች |
0.5 |
30,000.00 |
6 |
ሎት 5 |
አላቂ የፅዳት ዕቃዎች |
0.5 |
7,500.00 |
7 |
ሎት 6 |
ልዩ ልዩ ዕቃዎችና መሣሪያዎች |
0.5 |
2,000.00 |
8 |
ሎት 7 |
ልዩ ልዩ የጥገና ዕቃዎች /የቤት ቁሣቁስ/ |
0.5 |
7,500.00 |
9 |
ሎት 8 |
ልዩ ልዩ የጥገና ዕቃዎች /የመኪና ዕቃዎች/ |
0.5 |
1,875.00 |
10 |
ሎት 9 |
ቋሚ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች/ፈርኒቸር/ |
0.5 |
10,000.00 |
11 |
ሎት 10 |
ቋሚ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች/ኤሌክትሮኒክስ/ |
0.5 |
10,000.00 |
12 |
ሎት 11 |
ልዩ ልዩ አገልግሎቶች |
0.5 |
500.00 |
13 |
ሎት 12 |
ልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች የጥገና እና የሰርቪስ አገልግሎቶች |
0.5 |
1,500.00 |
14 |
ሎት 13 |
ልዩ ልዩ የጥገና እና የአገልግሎቶች ስራዎች |
0.5 |
500.00 |
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት ወረዳ 8 ሚሊኒየም ጤና ጣቢያ ስም የተዘጋጀ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በማስያዝ ወይም በዘረፉ ከተደራጁበት ወረዳ ጥቃቅንና አነስተኛ ጽ/ቤት የተፃፈ ህጋዊ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ አስራ አንደኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ታዛቢዎች ባሉበት የጨረታ ሠነድ መቀበያ ጊዜ የበቃ መሆኑን የሚገልፅ ቃለ ጉባኤ በመያዝ ተዘግቶ በዚያው ዕለት እና ሰዓት ከ30 ደቂቃ በኋላ 3፡30 የመክፈቻ ቃለ ጉባኤ ተይዞ ሲታሸግ የነበሩ ታዛቢዎች በተገኙበት ይከፈታል። በዚህ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲገኙ ይጋባዛሉ፤ ባይገኙ ግን የጨረታ መዝጊያውንም ሆነ መክፈቻ ቀኑን ወይም ሰዓቱን ማራዘም አይቻልም፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር፡- 0112-29-12-50 ወይም በኢሜይል
አድራሻችን፡- akw3hc@gmail.com ወይም ሊያገኙን ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡-ከአውቶብስ ተራ ወደ ሰባተኛ ወይም ከሰባተኛ ወደ አውቶብስ ተራ በሚወስደው አስፋልት መንገድ ሲሄዱ ከዋይ ዜድ ህንፃ ወደ መካነ ሠላም ሆቴል በሚወስደው መንገድ 200 ሜትር ያህል እንደሄዱ ባለ አራት ፎቅ ህንፃ ላይ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የወረዳ 8 ሚሊኒየም ጤና ጣቢያ በሚል ስያሜ ያገኙናል፡፡
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት
የወረዳ 8 ሚሊኒየም ጤና ጣቢያ