በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በወረዳ 12 ሳሎ የመ/ደ/ት ቤት የደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ህትመት፣ አላቂ የህክምና እቃዎች፣ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች እና የላቦራቶሪ እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ ልዩ ልዩ መሳሪያዎች እና መጽሐፎች፣ ለግብርና ለደን ለባህር ግብዓቶች፣ ማሽነሪና እድሳት ጥገና እቃዎች፣ ለጭነት የጉልበት፣ የጉልበት አገልግሎት፣ ለስልጠና አገልግሎት እቃዎች እና ቋሚ ዕቃዎች መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 07, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በወረዳ 12 ሳሎ የመ// ቤት በግልፅ ጨረታ በጨረታ ቁጥር 02/2018 ዓም የደንብ ልብስ ፤አላቂ የቢሮ እቃዎት ህትመት፤ አላቂ የህክምና እቃዎት፣ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች እና የላቦራቶር እቃዎች፤ የፅዳት እቃዎች፣ ልዩ ልዩ መሳሪያዎች እና መጽሐፎች፣ ለግብርና ለደን ለባህር ግብዓቶች፣ ማሽነሪና እድሳት ጥገና እቃዎች፣ለጭነት የጉልበት፣የጉልበት አገልግሎት፣ ለስልጠና አገልግሎት እቃዎች፣እና ቋሚ ዕቃዎች መግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት፡

ሎት1. 13,587.00 ሎት2. 10,342.00፤ ሎት3. 1,047.00፤ ሎት4. 298.00 ሎት5. 12,292.00 ሎት6. 15,397.00 ሎት7. 3,300.00 ሎት8. 90.00፣ሎት.9. 4,473.00 ሎት10 2,205.00፣ ሎት11, 2,250.00፣ ሎት12. 2,985.00፣ ሎት13 10,500.00 የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ /CPO/ በሎቱ መሰረት መቅረብ አለበት።

በዘርፉ የተሰማሩበት የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ማስረጃ እና የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣

  • የንግድ ስም ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣
  • ተጫራቾች የአንዱን ዋጋ ሲያቀርቡ /ቫት/ ደምረው ማቅረብ አለባቸው፣
  • በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  • በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NO/ ማቅረብ የሚችሉ
  • በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የዓመቱን ክሊራንስ ከግቢዎች ማቅረብ የሚችሉ፣
  • የጨረታ አሸናፊዎች ማሸነፋቸው በጹሁፍ የሚገለጽላቸው ሲሆን ለጨረታው አፈጻጸም ውል ማስከበሪያ ላሸነፉበት ጠቅላላ እቃ ዋጋ 10% CPO በማስያዝ ውል መዋዋል ግዴታ አለባቸው።
  • ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ቁሳቁስ ናሙና የሚቀርብባቸው እቃዎች በሳሎ የመ///ቤት /ግዥ ክፍል ማስረከብ አለባቸው።
  • የሚቀርበው ናሙና ለአንድ እቃ አንድ ናሙና ብቻ ነው።
  • የጨረታ ማስረከቢያ እና የውል ማስከበሪያ በደብዳቤ የሚያጽፉ ጥቃቅን እና አነስተኛ አቅራቢዎች የተሰማሩበት የንግድ ስራ መስክ ዘርፍ/ የሚገልጽ ደብዳቤ ካደራጃችሁ ተቋም ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • በእያንዳንዱ ሰነድ ገጽ ላይ የአቅራቢ ማህተም ማድረግ እና ዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝሩን የሚሞላው ኃላፊ በእያንዳንዱ ዋጋ በተሞላው የጨረታ ሰነድ ላይ በየገጹ መፈረም አለበት።
  • ለተጠቀሰው ዕቃ ዝርዝር የያዘው ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00ብር (ሁለት መቶ/ ብር ብቻ በመክፈል ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በት ቤቱ ፋግዥ ክፍል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በግልፅ በመሙላት ኦርጂናል እና ኮፒ በተለያ የፖስታ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በት/ቤቱ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ
  • በዋጋ መሙያው ሰንጠረዝ ላይ ስርዝ እና ድልዝ መኖር የለበትም
  • ግዥ ፈጻሚው አካል አሸናፊ ተጫራቾች በሚጠሩበት /በሚመረጡበት/ ጊዜ የገዛውን እቃ መጠን እንደ አስፈላጊነቱ እስከ (20%) ሃያ ለመቀነስ ወይም መጨመር ይችላሉ፡፡ ክፍያው የሚፈጸመው ሙሉ ለሙሉ በናሙና መሰረት ጥራቱ ሲረጋገጥ እና በንብረት ክፍል ገቢ ሲሆን ብቻ ነው።
  • ጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት 430 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ስላልተገኙ ተብሎ ጨረታው ሳይከፈት አይቀርም
  • መስሪያቤቱ የተሻለ ለዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • አድራሻ፡-አቃ/// ወረዳ 12 በካፍደም ፕላዛ በኩል በሚወስደው መንገድ አዲስ ሰፈር ነው።

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በወረዳ 12 ሳሎ የመ// ቤት