በደ/ኢ/ክ/መ/ግብርና ቢሮ የወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ በ2018 በጀት የተለያዩ እቃዎች እና አገልግሎቶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 07, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ቁጥር 001/2018

የጨረታ ማስታወቂያ

በደ////ግብርና ቢሮ የወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ 2018 በጀት ዓመት ለመማር ማስተማር አገልግሎት የሚውሉ

  • ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ
  • ሎት 2 የሰራተኞች ደንብ ልብስ
  • ሎት 4፤አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን
  • ሎት5 የእንስሳት መኖ ጥሬ ዕቃዎችን
  • ሎት 9፤የጓሮ አትክልት ዘሮችን
  • ሎት10 የህንጻ መሳሪያዎችን
  • ሎት12፤የግብርና ግብዓቶችን
  • ሎት13 የላብራቶሪ ዕቃዎችን
  • ሎት 14፤የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን
  • ሎት15፣ የእንስሳት መድኃኒቶችና ቁሳቁሶች
  • ሎት16 የእንስሳት ጤና መጽኃኒት
  • ሎት17 የኤሌክትሪክ ዕቃዎች
  • ሎት 18፤የስፖርት ዕቃዎችን
  • ሎት 19፤የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎትን

ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መሰፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት፤

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን የግብር ግዴታቸውን የተወጡ የተ.. ተመዝጋቢ የሆኑ የቲን ሰርተፍኬት/የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው ለተሸከርካሪዎች ጥገና አገልግሎት ከመንገድ ትራንስፖርት የታደሰ ደረጃ 3 እና ከዛ በላይ የብቃት ማረጋገጫ ፈቀድ ማቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለጨረታ ዶክመንቱ የማይመለስ ብር 150.00/አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ ብቻ በሶዶ ግብርና ኮሌጅ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተከፍተው በሚገኘው አካውንት ቁጥር 1000018208443 በማስገባት አድቫይስ በመያዝ ወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ ///አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 41 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  3. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ሲፐኦ ለእያንዳንዱ ሎት 1235፤11፤13141516 እና 17 ብር 30,000.00/ሰላሳ ሺህ ብር/ ለሎት 12፣እና፤9 ብር 15,000.00/ አስራ አምስት ሺህ) ብር ለሎት 49 እና 18 ብር 10,000.00/አስር ሺህ ብር/ከጨረታው ሰነድ ኮፒ ጋር አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ሰነድ አንድ ኦርጅናልና 1 የኦርጅናሉን ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በስም በታሸገ ኤምቨሎፕ ሙሉ አድርሻቸውን በመጥቀስ ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ መስገባት አለባቸው።
  5. የጨረታው ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው 16 የሥራ ቀን 400 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 430 ሰዓት ላይ ወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ ///አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 41 ይከፈታል፡፡16ኛው የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን ይከፈታል።
  6. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ላይ የማይነበብና ሰርዝ ድልዝ ያለው መሆን የለበትም።
  7. አሸናፊው ድርጅት የአሸናፋቸውን ዕቃዎች እስከ ከሌጁ ድረስ አቅርቦ ያስረክባል።
  8.  /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0465513984 መደወል ይቻላል፡፡

ወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ

ወላይታ ሶዶ