Your cart is currently empty!
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 የቀስተ ደመና አፀደ ህፃናት እና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 07, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ ጨረታ መለያ ቁጥር001/2018
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 የቀስተ ደመና አፀደ ህፃናት እና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1 አላቂየቢሮ እቃዎች CPO (15,000)
- ሎት 2 የጽዳት እቃዎች (CPO 10,000)
- ሎት 3 የደንብ ልብስ (CPO20,000)
- ሎት 4 የላብራቶሪ እና የህክምና እቃዎች (CPO 3,000 )
- ሎት 5 የተለያዩ ለጥገና የሚውሉ እቃዎች (CPO 15000)
- ሎት 6 የቋሚመገልገያ እቃዎች (CPO 20,000)
- ሎች 7. ህትመት (CPO 3000 )
- ሎት8. የኮሚፒውተር የፎቶ ኮፒ፣ማባዣ፣ጥገናና ሌሎች ስራዎች (CPO 2,000) –
በዚህ መሰረት ከላይ በተዘረዘሩት እቃዎች ላይ ጨረታ መሳተፍ የምትፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች በሙሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባችሁ።
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. በአቅራቢነት ሊስት የተመዘገቡ መሆናቸው።
3. የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው።
4. ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
5. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር( TIN) ያላቸው።
6.አምራች ሆነው በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ ከአደራጃቸው አካል የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
7. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት ማለትም ከሎት1-8 የሚሰላ ብር 2% በባንክ በተመሰከረለት የክፍያ ትዕዛዝ( CPO) ማስያዝ አለባቸው።
9 የጨረታው ሙሉ ሰነድ የማይመለስ ብር 200( ሁለት መቶ) ብር በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በቀስተ ደመና ቅ/መ/እና የመጀ/ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 14( ረዳት ፋይናንስ ቢሮ) በመምጣት ሰነዱን መውሰድ ይቻላል።
10. ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት አስር( 10) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በት/ቤቱ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር.15 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዋጋ የተሞላበትፋይናንሻል ሰነድ ዋናውንና ኮፒው ለየብቻቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒውን በማሸግ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
11. የጨረታ ሰነድ የመጨረሻው የአየር ላይ ቆይታው በአስረኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ይሆናል።
12. ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው ቀን ጠዋት 3፡30 ታሽጎ ወዲያውኑ በዕለቱ 4፡00 ሰዓት ላይ በት/ቤቱ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 15 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ ይከፈታል።
13. የጨረታው አሸናፊ አካል የውል ማስከበሪያ ላቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የውል ማስከበሪያ ሳያሲዙ ውል መዋዋል አይቻልም።
14. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ ሶስት ቀን በፊት ሳምፕል( ናሙና) ማቅረብ አለባችው፡ ፡ ሳምፕል ያላቀረበ ተጫራች ለውድድር አይቀርብም።
15. የጨረታው ሙሉ ሰነድ ሳይገነጠል መመለስ አለበት፡፡ ሙሉ ሰነድ ያላስገባ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይደረጋል።
16. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ያሸነፉትን ዕቃ በራሳቸው ትራንስፖርት ተቋሙ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
17. መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
18. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡– መሳለሚያ ወረዳ9 ከሞቢል 100 ሜትር ከፍ ብሎ እንገኛለን።
ለበለጠ መረጃ፡– 011 2 13 5068
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 የቀስተ ደመና አፀደ ህፃናት እና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት