Your cart is currently empty!
በየካ ክፍለ ከተማ በወረዳ 10 ት/ጽ/ቤት አንቆርጫ ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም በጀት አመት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 07, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001
በየካ ክፍለ ከተማ በወረዳ 10 ት/ጽ/ቤት አንቆርጫ ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም በጀት አመት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 የደንብ ልብስ
- ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች
- ሎት 3 አላቂ የትምህርት ዕቃዎች
- ሎት 4 የፅዳት እቃዎች
- ሎት 5 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች
- ሎት 6 ቋሚ እቃዎች ጥገና እቃዎች እና ቋሚ እቃዎች
በዚህ መሰረት በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች
1. በዘረፉ የተሰማሩ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
2. የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ
4. በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ
5. ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል የሚመለስ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ በእያንዳንዱ ሎት ማቅረብ የሚችሉ
6. ሎት 1 ብር 4000.00 (አራት ሺህ ብር ብቻ)
ሎት 2 ብር 4000.00 (አራት ሺህ ብር ብቻ)
ሎት 3 ብር 5000.00 (አምስት ሺህ ብር ብቻ)
ሎት 4 ብር 5000.00 (አምስት ሺህ ብር ብቻ)
ሎት 5 ብር 2000.00(ሁለት ሺህ ብር ብቻ)
ሎት 6 ብር 8,800.00 (ስምንት ሺህ ስምንት መቶ ብር) ማቅረብ አለባቸው።
7. ዝርዝር ጨርታውን የያዘውን ሰነድ የማይመለስ ሁለት መቶ /200.00 ብር/ በመክፈል ከት/ቤቱ የፋይናንስ ድጋፍ የስራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን እቃ ናሙና ለሚያስፈልገው ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖረባቸዋል።
9. ሳምፕል ለማምጣት አስቸጋሪ ከሆነ በፎቶ ማቅረብ ይቻላል።
10. ተጫራቾች ጨረታ አሸናፊው ውል ሲዋዋሉ የአጠቃላይ ያሸነፉበትን ብር 10% ውል ማስከበሪያ ማቅረብ ይኖረባቸዋል።
11. የጨረታው ሰነድ ኮፒና ኦርጅናል በመለየት በተለያየ ፖስታ አሽገው ሲመጡ ሲፒኦ ደግሞ ጨረታው ኦሪጅናል ባለበት ፖስታ ውስጥ በማስገባት አሽገው ማቅረብ ይኖረባቸዋል።
12. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ዝርዝር ሰነድ ላይ ባለው ዋጋ ማቅረቢያ በግልጽ ሞልተው ይህ ማስታውቂያ ከወታበት እለት ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 11:30 ድረስ ማስገባት ይኖረባችዋል።
13. የጨረታው ሳጥን ማስታወቂያ ከወጣበት በ11ኛው ቀን በ 4.00 ሰዓት ተዘግቶ :: በ11ኛው ቀን 4፡30 በት/ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ በፋይናንስ የስራ ሂደት ቢሮ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።
14. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡– ኮተቤ 32 ቁጥር ማዞሪያ ከፍ ብሎ አንቆርጫ ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ከፍ ብሎ
ስልክ 0118 664 718 / 19
በየካ ክፍለ ከተማ በወረዳ 10 ት/ጽ/ቤት የአንቆርጫ ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት