Your cart is currently empty!
በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የእድገት ጮራ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለቢሮና ለትምህርት አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 09, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የእድገት ጮራ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለቢሮና ለትምህርት አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች
- ሎት 1 የደንብ ልብስ ግዥ
- ሎት 2 ለአላቂ የቢሮ እቃዎች
- ሎት 3 ለህትመት
- ሎት 4 አላቂ የህክምና እቃ
- ሎት 5 ለአላቂ የት/ት እቃዎች
- ሎት 6 አላቂ የጽዳት ዕቃ
- ሎት 7 ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች
- ሎት 8 ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ
- ሎት 9 ለህንፃ ቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች ጥገና
- ሎት 10 የቋሚ ኤሌክትሪክ ጥገና
- ሎት 11 አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውን ዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሚያቀርብ፡፡
2. የገቢዎች እና ጉምሩክ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
3. ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት /ቫት/ የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4.የአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር መያያዝ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
5.ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ በአንድ ሎት 300/ ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ዕድገት ጮራ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
6. የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 1 ሎት2 ሎት 5 ሎት 6 ሎት 7 ሎት8፡ እነዚህ ሎቶች ለእያንዳንዳቸው 10,000 አስር ሺ ብር እንዲሁም ሎት 3 ሎት 4 ሎት 9 ሎት 10 ሎት 11 እነዚህ ሎቶች ለእያንዳንዳቸው 2000 ሁለት ሺህ ብር በባንክ በተረጋገጠ CPO ብቻ ማስያዝ አለበት፡፡
7. የመወዳደሪያ ዋጋው ከነቫት በማስቀመጥ በግልጽ ተጠቅሶ መጻፍ ይኖርበታል፡፡
የጨረታው ተሳታፊዎች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ፋይናንሺያል እና ቴክኒካል ዋናውንና ኮፒ በፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የሚወዳደሩበት ዕቃ ናሙና /specification/ ማቅረብ አለባቸው ፡፡ አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከታወቀ በኃላ በ15 ቀናት ውስጥ ከት/ቤቱ ጋር ውል መዋዋል አለበት፡፡
ተጫራቾች ያሸነፉበትን ደረጃውን የጠበቀ ዕቃዎችን ትዕዛዙ በደረሳቸው በአምስት የስራ ቀናት ውስጥ በናሙናው መሰረት አጠናቀው ለት/ቤቱ ንብረት ክፍል ሲያስረክቡና በጥራት ኮሜቴ ተፈትሾ ሲያልፍና በተቋሙ ኃላፊ ገቢ እንዲሆን ከታዘዘ በኋላ ይከፍላቸዋል፡፡
8. የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ11ኛው የስራ ቀን ጠዋት 4፡00 የጨረታው ሳጥን ይታሸግና በዛው እለት በ4፡30 ሰዓት ዕደገት ጮራ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋ/ግ/ንብ/አሥ/የቡድን መሪ ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
9. የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ሲታወቅ የውል ማስከበሪያ ካሸነፈበት ጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 10% በጥሬ ገንዘብ C.P.O ብቻ በቅድሚያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
11. አድራሻ ፡– ከአያት አደባባይ ወደ ጣፎ በሚወስደው መንገድ ገናዬ ማርያም ቤ/ክ መግቢያ ላይ ይገኛል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 0118 932 698 / 0118 931 407
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ዕድገት ጮራ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት