Your cart is currently empty!
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጋሞ ዞን የቁጫ አልፋ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ማቴሪያሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 09, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጋሞ ዞን የቁጫ አልፋ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ማቴሪያሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት-1፦ የሕንጻ መሳሪያዎች ግዥ፣
- ሎት-2፡– የጽሕፈት መሳሪዎች እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ግዥ፣
- ሎት-3፡– የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ፣
- ሎት-4፡– የቋሚ የቢሮ ዕቃዎች /ፈርኒቸር ግዥ/
- ሎት-5፦ የሞተር ሳይክል ግዥ
- ሎት-6፡– ጀነሬተር ግዥ
- ሎት-7፦ ለመንገድ ከፊታ አፈር ሥራ የዶዘር ማሽነሪ ኪራይ/ መኮናተር፣ ለወረዳው ዋና አስ/ር ጽ/ቤት G+1 ሕንጻ ግንባታ የሚውል ማቴሪያሎች፦
- ሎት-8፡– አሸዋ በቢያጆ፣ ጠጠር 02 በቢያጆ፣ የፍልጥ ድንጋይ በቢያጆ፣ የሙሌት ድንጋይ በቢያጆ፣ ብሎከት ባለ-20 ብቁጥር፣ ብሎኬት ባለ-15 በቁጥር እና ብሎኬት ባለ–10 በቁጥር
- ሎት-9፡– የሴ/መ/ቤቶች መኪኖች ጥገና ከነ መለዋወጫ ማቅረብ፣ የእናቶች ወሊድ አምቡላንስ ኮድ– 04266፣ የላንድ ኩሩዘር መኪና ታርጋ 30793፣ የቀይ መስቀል መኪና ታርጋ 02337፣ የሃይሉክስ መኪና ታርጋ 02156 እና የፖሊስ ፓትሮል መኪና ኮድ 0401 ጥገና ማድረግ፤
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ ተሻሽለው በወጣው በመንግስት ግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 70/2017 ዓ/ም መሰረት፡–
1. የ2018 ዓ/ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉበት መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. የግብር ከፋይነት ምዝገባ ቁጥር /Tin Number/ ያላቸው፡፡
4 የቫት ተመዝጋቢ የሆኑበት መረጃ አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. ከሽያጭ ዋጋ ላይ ለመንግስት ግብር 3% ለመክፈል ፈቃደኛ የሆኑ፡፡
6. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
7. የዕቃ አቅራቢነት በኦንላይን የተመዘገቡበትን ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
8. የጨረታ ሁኔታ በአይቴም ወይም በጥቅልል ሊሆን ይችላል፡፡
9. ለዶዘር ማሽን ሥራ እና ለመኪኖች ጥገና የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
10. ለዶዘር ማሸን ሥራ እና ለመኪኖች ጥገና ከመንግስት መ/ቤት የመልካም ሥራ አፈጻጸም ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
11. ተጫራቹ ለዶዘር ማሽን የግል ሊብሬ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
12. የጨረታውን ሰነድ ዋና እና ኮፒ በመለየት ኦርጅናሉንና ኮፒውን የጨረታ ሰነድ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በማስገባት በሰም በታሸገው ኤንቨሎፕ ፖስታ ውስጥ በማድረግ በቁጫ አልፋ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ-5 ላይ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
13. በጨረታ ሂደት ላይ አሸናፊ የሆነ ድርጅት ከጠቅላላ ዋጋ ላይ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ግዴታ አለበት፡፡
14. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አሥራ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ይሆናል፡፡
15. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ወደ ቁጫ ቁልፋ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቀጥር–5 ድረስ በመቅረብ የተዘጋጀውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
16. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ በጥሬ ወይም በቼክ 25,000.00/ ሃያ አምስት ሺህ ብር ብቻ/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተረጋገጠ ሕጋዊ CPO/ ከሚሳተፉበት ጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
17. የጨረታ ሣጥን የሚታሸገው የጨረታ ማብቂያ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡
18. ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወከሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
19. በጨረታው አሸናፊ ድርጅት ወይም ግለሰብ ዕቃውን እስከ ቁጫ አልፋ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ድረስ የጫኝ፣ አውራጅ እና የጭነት ወጪን በመሸፈን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
20. ተጫራቾች ወይም የጨረታ ወክል ያለመገኘት ጨረታውን መክፈት አያስተጓጓልም፡፡
21. የ16ኛው ቀን እሑድ ወይም በዓል ከሆነ ጨረታው በቀጣይ ሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፦
- ለዶዘር ማሽነሪ ኪራይ ሞዴል ከ2010 ዓ/ም ወዲህ ስሪት CAT D8R በአሁኑ ገበያ ያለ መሆን አለበት፡፡
- ለዶዘር ማሸነሪ የጭነት ዋጋ በአከራዩ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
- የዶዘር ማሸነሪ ጨረታ አሸናፊ ድርጅት ወይም ግለሰብ በውድድሩ ካሸነፈበት በሰባት/7/ቀናት ውስጥ ለአሰሪው መ/ቤት ማሸኑን የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- በጨረታው አሸናፊ ድርጅት ወይም ግለሰብ የዕቃው ከጥራትና ደረጃ ዝቅ ብል፣ ዕቃው ብጎድል፣ ከተዋዋለው የውል ጊዜው ብያልፍ በሕግ መሰረት ለመንግስት ከገባሁት ከጠቅላላ ውል ገንዘብ ላይ 20% የሚደርሰውን ብር ተቀጥቼ ገንዘብ ተመላሽ ለማድረግ በፍ/ህ/ቁጥር 2005 መሰረት የፀና ይሆናል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡– 09 16 66 99 82 / 09 26 36 60 87 / 09 76 13 56 48 / 09 84 66 61 89
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን የቁጫ አልፋ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት