የነቀምቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2018 ዓ.ም ትምህርትና ሥልጠና ዘመን ለሥልጠና ግብዓት የሚውሉ የኮንስትራክሽን፣ የፈርንኒቸር ዕቃዎች፣ የማሽን፣ የኤሌክትሮኒክስ፣ የኤሌክትሪካል፣ የአውቶ፣ የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት፣ የሠራተኞች ደንብ ልብስ፣ ኮምፕዩተርና የኮምፑዩተር ዕቃዎች እና የመኪና ጎማ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 09, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የነቀምቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 2018 . ትምህርትና ሥልጠና ዘመን ለሥልጠና ግብዓት የሚውሉ የኮንስትራከሽን የፈርንኒቸር ዕቃዎች፣ የማሽን፣ የኤሌክትሮኒክስ፣ የኤሌክትሪካል፣ የአውቶ፣ የጽሕፈት መሳሪያዎች የጽዳት የሠራተኞች ደንብ ልብስ፤ ኮምፕዩተርና የኮምፑዩተር ዕቃዎች እና የመኪና ጎማ ለመግዛት ስለምንፈልግ ከዚህ በታች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡ ተጫራቾች ማሟላት የሚጠበቅባቸው፡

1. በመስኩ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

2. የዘመኑ የገቢ ግብር የተከፈለበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ( VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN NUMBER) ያላቸው፤

4. የአቅራቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤

5. ማንኛውም ተጫራች ከመንግስት ግዥ ያልታገደ መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ አለበት፤

6 አቅራቢዎች ተጫርተው ያሸነፉትን ዕቃ በራሳቸው ትራንስፖርት እስከ ነቀምት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ድረስ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡

7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዕቃ ጥራት ያለውና ደረጃውን የጠበቀ መሆን አለበት፤

8. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኃላ መተው ወይም ሌላ ሀሳብ ማቅረብ በፍፁም አይችሉም፡፡

9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ) ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርበታል፤

10. ጨረታውን ለማደናቀፍ የሞከረ ማንኛውም ተጫራች መንግስት ከሚያወጣው ጨረታ ውጭ ይሆናል፤

11. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ሰነድ የማይመለስ ብር 500(አምስት መቶ) ከፍሎ፣ ነቀምቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 በሚገኘው ክፍል መውሰድ ይችላል፡፡

12. አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡

13. ማንኛውም ተጫራች አሸናፊ መሆኑ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ 10 ቀን ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ውል መቀበል አለበት፡፡

14. ከዚህ በፊት ማለትም ኮሌጃችን ባወጣው ጨረታ 2017 . በግልጽ ጨረታውን ካሸነፉ በኃላ ዋጋ ስለጨመረ ዕቃዎቹን አናቀርብም በሚል ምክንያት ሲፈጥሩ የነበሩ ተጫራቾች በዚህ ጨረታ ላይ መሳተፍ አይችሉም፡፡

15. ተጫራቾቾ ዕቃዎቹን ዋጋ ዝርዝር የተጠየቀውን “specification” ሳይለውጡ የጨረታውን መወዳደሪያ ሰነድ ላይ ዋጋውን ከነ ተጨማሪ እሴት ታክስ በመሙላት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

16. የተጠየቀው “specification” በባዶ ቦታ ላይ በትክክል ሞልተው ያላቀረቡና ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም

17. ተጫራቾች የገዙት ሰነድ ዋጋውን ከሞሉ በኃላ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ ተደረጎበት ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻ በሁለት ኤንቨሎፕ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

18. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን 400 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ከታሸገ በኃላ በዛው ዕለት ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጠዋት 415 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ቀኑ አመት በዓል ቅዳሜ ወይም እሑድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡

19. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

20. ሰነዱ ገቢ የሚደረግበትና የሚከፈትበት ቦታ ነቀምቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 ክፍል ይሆናል፡፡

አድራሻ

ነቀምቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 4

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች

09 86 07 46 36 / 057 661 2454 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል

በኦሮሚያ የሥራ ዕድል ፈጠራና ሙያ ቢሮ የነቀምቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ