Your cart is currently empty!
የድሬዳዋ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ግዢና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 2018 በጀት ዓመት የሚኒባስ የመኪና ኪራይ አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Melekite Dire(Sep 17, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሚኒባስ መኪና ኪራይ ግልፅ ጨረታ
የድሬዳዋ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ግዢና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የሚኒባስ የመኪና ኪራይ አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- የሚኒባስ የመኪና ኪራይ
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር / TIN No / ያላቸው
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑትን
- በዘርፉ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል
- በድርጅቱ ባለቤቱ ስም የታተመ ቁጥር ያለው ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል
- የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው /ያላት
- የታክሲ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- መልካም የሥራ አፈፃፀም አንድ ዓመትና ከዚያ በላይ ማቅረብ የሚችል
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50.000 / ሃምሣ ሺ ብር በጥሬ ገንዘብ/ በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ የሚችሉ
ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በድሬ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት የሚቆይ ሆኖ በጨረታ መሳተፍ የምትፈልጉት ዘወትር በሥራ ሰዓት በድሬዳዋ አስተደደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ግዢ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 303 3ኛ ፎቅ በመቅረብ የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 / አምስት መቶ ብር / በመግዛት የሚጫረቱበትን ዋጋ ሞልተው በታሸገ ኤንቨሎኘ በማድረግ በጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር ይችላሉ፡፡
የጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት ታሽጐ በእዛው እለት ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙት በመሬት ልማትና ማንጅመንት ቢሮ ግዢና ፋይናንስ ንብረት አስተደደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 303 3ኛ ፎቅ ይከፈታል፡፡
ሆኖም የጨረታ መክፈቻው ቀን በበዓል ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡– 09 10 25 82 50/09 20 42 92 ደውሎ ማጠየቅ ይቻላል፡፡