Your cart is currently empty!
በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የተለያዩ የመገልገያ ዕቃዎችና ለምርት አገልግሎት የሚውሉ የምርት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 20, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨ.ሰ.ቁ:-NCB-AAMMI-001/2018
በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ለ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ለሠራተኛ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የመገልገያ ዕቃዎችና ለምርት አገልግሎት የሚውሉ የምርት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት-1 የስቴሽነሪ ዕቃዎች
- ሎት-2 የጽዳት ዕቃዎች
- ሎት-3፡- የአደጋ መከላከያ እና የሥራ አልባሳት
- ሎት4፡-የምርት ቀለምና ኬሚካል ፈሳሾች
- ሎት-5፡- የትራክተር ራዲያተር ኮር
- ሎት 6፡- የምርት ግብዓት ጥሬ እቃ
- ሎት-7፡- የትራክተር እና የፓምፕ መለዋወጫ
- ሎት 8 የትራከተር ጎማዎች
- በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ያህል ሰነዱን አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 014 በመገኘት መውሰድ (መግዛት) ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት እቃ ጋር ተዛማጅ የሆነ በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፊቃድ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣ የተጨማሪ እሴት ታከለ የምዝገባ የምስከረ ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የግብር ከሊራንስ /ጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የሚያስችል ምዝገባ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተወዳዳሪዎች በጨረታው ላቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በተጫራቹ ምርጫ ከሚከተሉት ዓይነቶች አንዱ ሊሆን ይችላል፡፡
- (ሀ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና፣
- (ለ) በጥሬ ገንዘብ ወይም በታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼከ ወይም የክፍያ ትዕዛዝ/CPO/ የባንከ ጋራንቲው 60 ቀንና ከዚያ በላይ መሆን አለበት
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ( አስር) የሥራ ቀናት በአዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በግዢ ከፍል ቢሮ ቁጥር 04 በመገኘት ሰነዱን በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተገለፀው አስተሻሸግ መሰረት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር ) የሥራ ቀናት አየር ላይ የሚውል ሆኖ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከረፋዱ 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በተገለፀው አድራሻ በአዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የስብሰባ አዳራሽ ጨረታው ይከፈታል፡፡ ቀኑ የበዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል፡፡ የተጫራች አለመኖር ፖስታው ተሟልቶ እስከተገኘ ድረስ ጨረታውን ለመክፈት እያስተጓጉልም።
- ኢንዱስትሪው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 022 111 0689/ 09 12 26 46 80 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡ አዳማ ከወንጂ ማዞሪያ ተቃራኒ አቅጣጫ 500 ላይ
ስልክ ቁጥር፡- 022 111 0689/ 009 12 26 46 80 ፋክስ፡- 022 111 1866 አዳማ
በኢትዮ-ኢንጅነሪንግ ግሩፕ አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ
cttx Agriculture and Farming cttx, cttx Chemicals and Reagents cttx, cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Equipment cttx, cttx Installation, cttx Laboratory Equipment and Chemicals cttx, cttx Machinery and Equipment cttx, cttx Mechanical cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Products and Services cttx, cttx Pumps, cttx Raw Materials and Supplies cttx, cttx Raw materials cttx, cttx Safety and Security cttx, cttx Shoes and Other Leather Products cttx, cttx Spare Parts and Car Decoration Materials cttx, cttx Stationery cttx, cttx Textile, Electromechanical and Electronics cttx, Garment and Leather cttx, Garments and Uniforms cttx, Maintenance and Other Engineering Services cttx, Motors and Compressors cttx