የድሬዳዋ አስተዳደር አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ክላስተር ልማት ኮርፖሬሽን በማኑፋክቸሪንግ ሼድ ፕሮጀክት 3 የተገነቡ ሼዶችን የኤሌትሪክ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ የኤሌትሪክ ማቴሪያሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 22, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡///ኮርፖሬሽን 03/2018 .

የድሬዳዋ አስተዳደር አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋከቸሪንግ ኢንዱስትሪ ክላስተር ልማት ኮርፖሬሽን በማኑፋክቸሪንግ ሼድ ፕሮጀክት 3 የተገነቡ ሼዶችን የኤሌትሪክ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ የኤሌትሪክ ማቴሪያሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት፡

በዘርፉ 2017 . የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር Tin No/ ያላቸው፤ የቫት ከፋይነት ሰርተፊኬት ያላቸው፤ በአቅራቢነት ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ ሆኖ የምስክር ወረቀት ያላቸው፤

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ፣ ሲፒኦ ወይም ካሽ ከመወዳደሪያ ዋጋቸው ጋር አያይዘውና አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ከፍለው በመውሰድና ዋጋ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በድሬዳዋ አስተዳደር አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ክላስተር ልማት ኮርፖሬሽን ቢሮ ዲፖ ገበያ ማዕከል 3 ፎቅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 06 ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

ጨረታው በ16ኛው ቀን 330 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት 400 ሰዓት ላይ ይከፈታል። ነገር ግን የጨረታው መክፈቻ ቀን በእረፍት ቀን ወይም በበዓል ቀን ከዋለ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል

ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው እና ውል ከፈፀሙ በኋላ በ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ጊዜ ውስጥ አጠናቀው የመ/ቤቱ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።

ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፡– 025-4-11-15-74/ 09-20-89-41-42

በድሬዳዋ አስተዳደር የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ክላስተር ልማት ኮርፖሬሽን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *