Your cart is currently empty!
በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ ሆሚቾ አሙኔሽን ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 24, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ ሆሚቾ አሙኔሽን ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ከዚህ በታች ከሎት1-10 የተዘረዘሩትን የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1 የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች
- ሎት 2 –የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች
- ሎት 3 –የተለያዩ የሴፍቲ ዕቃዎች
- ሎት 4- የተለያዩ ጥሬ ዕቃዎች
- ሎት 5 –የተለያዩ ኬሚካሎች
- ሎት 6 የተለያዩ ዘይት እና ቅባት
- ሎት 7-የተለያዩ የተሽከርከሪ ጎማዎች
- ሎት 8-የተለያዩ ማሽነሪዎች
- ሎት 9-ተሽከርካሪ ግዥ
- ሎት 10-የተለያዩ ባትሪዎች
በመሆኑም ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድረን ለመግዛት ስለምንፈልግ፤
ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና በመንግስት ዕቃ ግዥ አቅራቢነት የተመዘገቡ የሆኑና፡–
1. የወቅቱን ግብር ያጠናቀቁ
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT 15% ከፋይነት የተመዘገቡ ምስክር ወረቀት መኖሩን
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No) ያላቸው
4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ዋና እና ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች በአራት ቅጂዎች ማቅረብ አለባቸው 1ኛ ቅጂ ላይ ኦርጅናል ቴክኒካል ዶክመንት፤2ኛ ኦርጅናል ፋይናንሻል ዶክመንት፤3ኛ ኦርጅናል ቴክኒካል ዶክመንት ኮፒ እና 4ኛ ኦርጅናል ፋይናንሻል ዶክመንት ኮፒ በማለት በሁለተኛው ቅጂ ላይ “ኮፒ” የሚል ምልክት በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
6.ማንኛውም ተጫራች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ የተጫራቹ ወይም የሕጋዊ ወኪሉ ፊርማና የድርጅቱ ማህተም መስፈር አለበት፡፡ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታው ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ሰነዱም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 200( ሁለት መቶ ብር) በመግዛት ዝርዝሩን ሞልተው ማቅረብ ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋ 2,000,000.00 በCPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
8. ቅጂዎች ማለትም ዋና እና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተገለፀው አድራሻበተዘጋጀው ሣጥን ማስታወቂያው ከወጣበትቀንጀምሮ ከ14/01/2018 እስከ 04/02/2018 ዓ.ም ድረስ መግዛት እና ማስገባት አለባቸው፡፡
9. ጨረታው በ 05/02/2018 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ከእስፔሲፊኬሽንውጪ የሆነ ዕቃ የሚያቀርቡ ተጫራቾች ተቀባይነት የሌለው ከመሆኑም በላይ በዚህ ምክንያት ለሚደርሰው ኪሣራ ተጠያቂ ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡– የልማት ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የጨረታ ሰነዱን እና የጨረታ ሳጥኑ የሚገኘው አምቦ ምዕራብ ሸዋ ዞን አስተዳደር
በተዘጋጀው ጊዜያዊ ቢሮ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0919 203 368 / 0920 944 104 / 0969 391 969 ወይም +251 11-2-19-00-42 ይደውሉ፡፡
በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የሆሚቾ አሙኔሽን ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ