Your cart is currently empty!
በድሬዳዋ አስተዳደር ጎሮ ጤና ጣቢያ 2018 ዓ/ም በጀት አመት መድሃኒት አቅራቢ ድርጅቶችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል
Addis Zemen(Oct 02, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
በድሬዳዋ አስተዳደር ጎሮ ጤና ጣቢያ 2018 ዓ/ም በጀት አመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግዥዎችን ለመፈፀም አቅራቢ ድርጅቶችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል
ከዚሁ መሰረት በጨረታው ላይ ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች።
- 4ተኛ /ሎት አራት/ መድሃኒት
1.1 ተጫራቾች በዘረፍ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ በተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
1.2 በመንግስት ግዥ አቅራቢ የተመዘገቡና የተመዘገቡበትን ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
1.3 ተጫራቾች የታክስ መለያ ቁጥር (TIN No) ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
1.4 ተጫራቾ የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሠዓት ለ 15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል በጎሮ ጤና ጣቢያ በግዥ/ፋ/ን/አስ/ድ የሥራ ሂደት ቢሮ አንደኛ ፎቅ በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
1.5 መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 5000/አምስት ሺ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት CPO ወይም (BI BOND) በጨረታው ኦርጅናል ሰነድ ጋር ኢያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
1.6 ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሠነድ መቀበያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
1.7 የጨረታ ሰነዱ የሚከፈትበት ቀን ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናት ከቆየ በኃላ በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል።
1.8 የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በፁሁፍ እንደተገለጸለት አስፈላጊውን የጨረታ ውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከጤና ጣቢያው ጋር ውል መፈራረም አለበት።ይህ ባይፈፀም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
1.9 ተጫራቾች ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን እና ፊርማቸውን እንዲሁም የተሟላ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
ማሳሰቢያ፡– ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማስረጃ፡– በድሬዳዋ አስተዳደር ጎሮ ጤና ጣቢያ መደወል ይቻላል።
025 211 1756 (0910 595 368)
በድሬዳዋ አስተዳደር ጎሮ ጤና ጣቢያ