የድሬዳዋ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ግዢና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማች እቃዎች ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Melekite Dire(Oct 01, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ የጨ/መ/ቁ/መ/ል/ማ/ቢሮ 004/2018

የድሬዳዋ አስተዳዳር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ግዢና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ለ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማች እቃዎች ጥገና  በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎች እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡

  1. 2018 በጀት አመት በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ 
  2.  የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN NO / ያላቸው 
  3.  የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ 
  4.  የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው 
  5.  የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው 
  6.   የዘመኑን ግብር የከፈለበት ማስረጃ / ታክስ ክሪላንስ / ማቅረብ የሚችሉ
  7.  የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ / CPO  / ማስያዝ የሚችሉ
  • ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በድሬ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት በድሬዳዋ አስተዳደር መሬት ልማትና ማነጅመንት ቢሮ ግዢ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 304 በመቅረብ የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመግዛት የሚጫረቱበትን ዋጋ ሞልተው በታሸገ ኤንቨሎኘ በማድረግ ለጨረታው በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር ይችላሉ፡፡
  • ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት ታሽጎ በዛው እለት ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ግዢና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 304 3ኛ ፎቅ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የጨረታ መክፈቻ ቀን በበዓል ቀናት ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥር 09 -20-42-33-92  /09 -10 25 82 50 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ ፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ግዢና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *